
ሁመራ፡ ጥር 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ለሰላሳ ዓመት በሰቆቃ፣ በግፍና በደል ተጠፍራ የቆየችው የወልቃይት ጠገዴ ምድር ነፃነቷን ከተጎናፀፈች በኃላ ለሁለተኛ ጊዜ የጥምቀትን በዓል ሴቶች በባህላዊ ልብስ አጊጠው፣ ህፃናት የክት ልብሳቸውን ለብሰው፣ ቀሳውስት ልብሰ ተክህኖአቸውን ተጎናፅፈው፣ ዘማሪያን ያሪዳዊ ዝማሬን እያዜሙ፣ ወጣቶች በጭፈራ፣ ሴቶች በእልልታ የጥምቀትን በዓል በሁመራ በድምቀት እያከበሩ ነው።

በበዓሉ ላይ ያገኘናቸው ዶክተር ገሰሰው ወንድም የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ አማረኛ በመናገሩ የአባቶቹን እሴት እንዳያስቀጥል ከፍተኛ ጫና ሲደርስበት እንደነበረ ገልጸዋል። ዛሬ ላይ እንዲህ በአማረኛ እየጨፈርን እየዘመርን የነፃነት ጥምቀታችን ማክበራችን ትልቅ ድል ነው ብለዋል።
ብዙዎች ለኛ ነፃነት ተሰውተዋል፤ ብዙዎች ስለነፃነታችን ቆስለዋል፤ ደምተዋል በእነሱ መስዋእትነት ዛሬ ላይ እኛ ቁመናል ማንነታችንን አስመልሰናልና ክብርና ሞገስ ይገባቸዋል ነው ያሉት።
“የወልቃይት የግፍ በደል ተደምስሷል እኛም በቋንቋችን ነግሰናል” ያለን ደግሞ ወጣት አምሳለ ተስፋየ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ በቋንቋው በዓሉን በማክበሩ መደሰቱን ተናግሯል።

ምዕመኑ የወገን ጦር አባላትን በማመስገን ጀግንነታቸውን በሽለላ በቀረርቶና በጭፈራ በማሞገስ ያላቸውን ክብር ገልፀዋል።

ምዕመኑም በነቂስ ወጥቶ ታቦታቱን በማጀብ ከማደሪያቸው ወደየ አድባራታቸው በማስገባት የጥምቀትን በዓል በደማቅ ሁኔታ ሲያነግሱ ውለዋል።
ያየህ ፈንቴ ከሁመራ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
