
ደብረብርሃን፡ ጥር 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጥምቀት በዓል በደብረብርሃን ሃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓቱን ጠብቆ በድምቀት እየተከበረ ነው። ታቦታቱ ከማደሪያቸው አጼ ዘረዓ ያዕቆብ ስታዲየም ወደ መንበራቸው ተመልሰዋል።
በዓሉ ታቦታት ባደሩበት በሕረ ጥምቀት ከሌሊቱ ጀምሮ ስርዓተ ቀዳሴው ተከናውኖ ባህረ ጥምቀት ከተባረከ በኋላ የጥምቀት ሥነ ስርዓቱ ተጠናቆ ታቦታቱ ወደየአጥቢያ ቤተክርስቲያናት በካህናትና በምእመናን ታጅበው ነው የተመለሱት።
በዓሉ በሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን ዝማሬ፣ ካህናትና ዲያቆናት በቅዳሴና በሽብሸባ እናቶች በእልልታ፣ ወንዶች በሆታ፣ ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች በባህለዊ ጭፈራዎች ሃይማኖታዊና
ባህላዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እየተከበረ ነው።
በበዓሉ ላይ ወጣቶች ታቦታት የሚሄዱበትን ከማፀዳት ጀምሮ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅተው ኀላፊነታቸውን እየተወጡ ነው::
በሥነ ጊዮርጊስ ከበደ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
