
ጎንደር: ጥር 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ2014 ዓ.ም ጥምቀትን ስናከብር መለያየትን በአንድነት፣ ጥላቻን በፍቅር፣ መፍረስን በመገንባት፣ ክፋትን በደግነት፣ ተንኮልን በቀናነት ድህነትን በብልጽግና ድል በማድረግ ሊሆን እንደሚገባ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ ተናግረዋል፡፡
ሀገራችንን የገጠማትን ችግር ለመቅረፍ በውስጥም በውጭም የምንገኝ ኢትዮጵያውያን በአንድነት በመቆማችን የመከራውን ዘመን አልፈን ጥምቀትን እንዲህ ባማረ ሁኔታ ማክበር ችለናል፤ ለዚህም ምስጋና ይገባል፤ ይህንን ቅንጅት በልማቱ መድገም እንደሚገባ ነው የገለጹት፡፡
የ2014 ዓ.ም የጥምቀት በዓል የመከራው ቀን በተባበረ ክንድ ተደምስሶ በተወገደበት፣ የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ወደ ሀገራቸው የመጡ የቁርጥ ቀን ልጆች በተገኙበት የሚከበር በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው፡፡
ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ቡድን በመደምሰስ የጎንደር ሕዝብ በደማቅ ቀለም በታሪክ የሚመዘገብ ሥራ ሠርቷል፤ ለዚህም ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡
ጎንደር የአንድነት እና የሰላም ተምሳሌት መኾኗን ተረድተን ታሪኳን የሚመጥን ኢኮኖሚ ታስመዘግብ ዘንድ የሁላችንንም ርብርብ ይጠይቃል ነው ያሉት፡፡
ለጎንደር ከተማ ዘላቂ ሰላም በአንድነት እና በሕብረት መሥራት ተገቢ መሆኑንም አቶ ዘውዱ ገልጸዋል፡፡
በትርንጎ ይፍሩ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
