አቢሲኒያ ባንክ በአማራ ክልል የመጀመሪያውን የቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት ማዕከልን በጎንደር ከተማ አስመርቆ ለአገልግሎት አበቃ።

323

ጎንደር፡ ጥር 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አቢሲኒያ ባንክ በአማራ ክልል የመጀመሪያውን የቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት ማዕከልን በጎንደር ከተማ አስመርቆ ለአገልግሎት አብቅቷል። ቴክኖሎጂው ፈጣን እንዲሁም ዘመናዊ አገልግሎት ያስችላል ተብሏል፡፡

አቢሲኒያ ባንክ ያስመረቀው የቨርቹዋል ባንክ አካላዊ ርቀትን ጠብቆ ለማስተናገድ እንደሚያስችል በአቢሲኒያ ባንክ የባሕር ዳር ዲስትሪክት የፕላኒንግ ኦፊሰር አቶ ማስተዋል ማረጉ ገልጸዋል፡፡ ይህም በሌሎች ቅርንጫፍ ባንክ ብቻ ሲሰጥ የነበረውን አገልግሎት በተሻለ ለመስጠት ያስችላል ተብሏል። በዚህ ማሽንም አዲስ ሒሳብ መክፈትን ጨምሮ፣ ቼክ መዘርዘር፣ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት፣ በባንኩ ከሚገኝ ሒሳብ ወደ ሌላ ሒሳብ እንዲሁም ወደ ሌሎች ባንኮች ወደሚገኝ ሒሳብ መላክ እና ማዘዋወርን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችንም ለመስጠት ያስችላል ብለዋል አቶ ማስተዋል።

በተጨማሪም የውጭ ሀገር የገንዘብ ኖቶችን በደምበኞች የውጭ ምንዛሬ ሒሳብ ላይ ገቢ ለማድረግ ያስችላል ነው ያሉት።

በአቢሲኒያ ባንክ የባሕር ዳር ዲስትሪክት ማናጀር አቶ ዮሴፍ ዓለሙ ባንኩ ለደንበኞች የዘመነ አገልግሎትን ለመገንባት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በክልሉ የመጀመሪያ የሆነውን የቨርቹዋል የባንክ ማዕከል መገንባቱን ተናግረዋል። በቀጣይም የቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት ባንኩ እየሠራ መሆኑን አመላክተዋል።

ዘጋቢ፡- ቃልኪዳን ኃይሌ- ከጎንደር

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ዜጎች ሁሉ ተዋደው በመሥራት ከድህነት መውጣት አለባቸው” ብፁዕ አቡነ አብርሃም
Next article“ችግሮቻችን በጉልበት ብቻ ሳይሆን በብልጠትም የሚፈቱ ናቸው፤” የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)