“ዜጎች ሁሉ ተዋደው በመሥራት ከድህነት መውጣት አለባቸው” ብፁዕ አቡነ አብርሃም

234

ባሕር ዳር፡ ጥር 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የከተራ በዓል በባሕር ዳር በድምቀት እየተከበረ ነው። ታቦታቱ ከየአድባራቸው ወጥተው በጥምቀተ ባሕር ማደሪያቸው ደርሰው ሊቃውንት በዝማሬ፣ ምዕመናኑ በሆታና በእልልታ በዓሉን እያከበሩ ነው። በበዓሉ ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባልና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የበደሉ ሰዎች ከሐጢያታቸው ነፃ እንዲሆኑ ንስሐ መግባት እንዳለባቸው መክረዋል። ሰው የራሱን እንጂ የሰውን መመኘት እንደሌለበትም አስተምረዋል። ለንስሐ የሚያበቃውን ፍሬ ሥሩ ነው ያሉት።

በሴራ፣ በግድያ፣ በማፈናቀል፣ በመዝረፍ የተቀረጸ ትውልድ ተፈጥሯል ያሉት ብፁዕ አቡነ አብርሃም ከዚህ ሐጢያት ሁሉ ነፃ መሆን የሚቻለው ንስሐ ስንገባ ብቻ ነው ብለዋል። በዘመናችን ለምን እግዚአብሔርን አምልከሃል፣ ስሙንም ለምን ጠርተሃል የሚሉ ትውልዶች ስለተፈጠሩ እግዚአብሔር ልቦናውንና ማስተዋልን ይስጣቸው ብለዋል። ለዚህም ቤተክርስቲያን ትጸልያለች ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ከጥንት ጀምሮ የሕዝብን አንድነት በመጠበቅ፣ አብሮ መብላትና አብሮ መጠጣትን እንጂ ጥላቻን አላስተማረችም። ቤተክርስቲያን ክብሯ እንዲጠበቅ ተከታዮቿ ሁሉ አንድ መሆን እንዳለባቸውም መክረዋል። ለሀገር መሰረት የሆነችውን ቤተክርስቲያንን ማክበር እንደሚገባም ብፁዕ አቡነ አብርሃም አሳስበዋል።

ትውልዱ በመልካም ሥነ ምግባር መታነጽ እንዳለበት ብፁዕ አቡነ አብርሃም መክረዋል።

ዜጎች ሁሉ ተዋደው በመሥራት ከድህነት መውጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ኅብረተሰቡ መረጃን ሳያጣራ መከተልም ሆነ መቀበል እንደሌለበትም አሳስበዋል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleምዕመኑ ያንን ሁሉ መከራ አሳልፎ ለዚህ በመብቃቱ እንኳን ደስ አላችሁ ሲሉ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ገለጹ፡፡
Next articleአቢሲኒያ ባንክ በአማራ ክልል የመጀመሪያውን የቨርቹዋል ባንኪንግ አገልግሎት ማዕከልን በጎንደር ከተማ አስመርቆ ለአገልግሎት አበቃ።