
ጎንደር፡ ጥር 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትምሕርት ሚኒስቴር በትምሕርት ጥራት ማስጠበቅን በተመለከተ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ጋር እየመከረ ነው። የትምሕርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኢትዮጵያ የትምሕርት ሥርዓት ግቦችና ይዘውት የመጡትን አዎንታዊና አሉታዊ ውጤቶች በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል።
ባለፉት ዓመታት የትምሕርት ሥርዓቱ ለሽፋን የሰጠውን ያክል ለጥራት ትኩረት አለመስጠቱ፣ ትምሕርት ቤቶች የፖለቲካ ማራመጃ ማዕከላት መሆናቸው፣ ብቁ ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ መፍጠራቸውን አንስተዋል።
በትምሕርት ሥርዓቱ አተገባበር ወጥነት አለመኖር፣ በግልና በመንግሥት የትምሕርት ተቋማት ላይ የትምሕርት አሰጣጥና አተገባበር መለያየት በተጨማሪም ችግር ፈች ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ሂደት ላይ እንቅፋት እየፈጠሩ መሆኑን አብራርተዋል።
ሚኒስትሩ እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ትምህርት ሚኒስቴር በሁሉም አካባቢዎች ጥራት ያለው ትምህርት እውን ለማድረግ እየሠራ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት። “ሀገራችን ያሉ የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምሕርት በመስጠት ብቁ ዜጋ መፍጠር እስካልቻሉ ድረስ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች አንከፍትም” ሲሉም ለትምሕርት ጥራት በቀጣይ ሊሰጠው የሚችለውን ትኩረት አስረድተዋል።
የውይይቱ ተሳታፊ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምሁራንም በትምሕርት ዘርፉ በሀገሪቱ ለዓመታት የዘለቀውን ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴሩ እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡ የሚታዩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ የበኩላቸውን እንደሚወጡም አሳውቀዋል።
በውይይቱ የትምሕርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡-ኃይሉ ማሞ-ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
