በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዝርፊያና ውድመት የደረሰበት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ወደ ሥራ ተመለሰ፡፡

139

ጥር 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዝርፊያና ውድመት የደረሰበት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ በከፍተኛ ርብርብ ወደ ሥራ መመለሱን የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሰኢድ ገልፀዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዲሰጥ ታስቦ በ93 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ላለፉት ዓመታት ለበርካታ ዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር እና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት የራሱን ድርሻ ሲወጣ የነበረ ፓርክ ሲሆን በወራሪው እና ሽብርተኛው የትግራይ ቡድን ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡
ሥራ አስኪያጁ አቶ አህመድ አንደገለፁት ሁሉም የሚመለከተው የመንግሥት እና የኅብረተሰብ አካል በእልህ እና በቁጭት በመሥራት ለሥራ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች ተሟልተው እና መሰረተ ልማቶች ተጠግነው ፓርኩ አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡

በፓርኩ ውስጥ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎችን ለማሳለጥም በአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ስር የሚገኙ እንደ ባንክ፣ ጉምሩክ እና ሌሎችም ሴክተሮች ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሰኢድ መግለጻቸውን ከኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ፓርኩ የደረሰበትን ከፍተኛ ጉዳት በማስተካከል በአጭር ጊዜ ወደ ሥራ እንዲመለስ በማድረጉ ሂደት የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ የፓርኩ ሠራተኞች፣ የባለሃብቶች ቁርጠኝነት፣ የተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ድጋፍ ፣ የአካባቢው ማኅበረሰብ እና የጸጥታ ሃይሎች ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡
አሁን ላይ ወደሥራ የገቡ የአምራች ድርጅት ሠራተኞች ወደ ማምረት ሂደት በአፋጣኝ የገቡ ሲሆን ሌሎች በሂደት ላይ የሚገኙ አምራች ድርጅቶችም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ በመግባት በቅርቡ ወደ ውጭ መላክ ለመጀመር እቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑ ታውቋል፡፡

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት እና ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባ ሲሆን አሁን ላይ በፓርኩ ኢንቨስት ማድረግ ለሚፈልጉ የሀገር ውስጥም ይሁን የውጪ ሀገር ባለሀብቶች ምቹ ሁኔታዎች እንደተመቻቹ ለማወቅ ተችሏል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleለኢክራም የመኖሪያ ቤት እና የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገላት፡፡
Next article“ሀገራችን ያሉ የከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ጥራት ያለው ትምሕርት በመስጠት ብቁ ዜጋ መፍጠር እስካልቻሉ ድረስ አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች አንከፍትም” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ