
ጥር 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ታጣቂዎች ተደፍራ በጽናት አደባባይ ወጥታ “የደፈሩኝ ይፈሩ” ስትል የደረሰባትን ግፍ ለዓለም ያጋለጠችው ታዳጊዋ ኢክራም ያሲን የመኖሪያ ቤት እና የገንዘብ ድጋፍ ተደረገላት።
ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ሲያደርጉላት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደግሞ የመኖሪያ ቤት ለታዳጊዋ አበርክቶላታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከንቲባዋ አዳነች አበቤ አማካኝነት ለታዳጊዋ የመኖሪያ ቤቱን ቁልፍ አስረክበዋታል።
ታዳጊ ኢክራምና ቤተሰቦቿ እስከዛሬዋ ቀን ድረስ በባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ድጋፍ ሲደረግላት የነበረ ሲሆን፤ ላለፈው አንድ ወር በኢትዮጵያ ሆቴል ሙሉ ወጪያቸው በአቶ በላይነህ ተሸፍኖላቸው ቆይታ አድርገዋል።
ባለሀብቱ በተጨማሪም ኢክራምን ከልጆቻቸው እንደ አንዷ በመቁጠር እንደሚያስተምሯት ቃል መግባታቸው፤ ለታዳጊዋ እናት ወይዘሮ ጠይባም የሥራ ዕድል እንደሚያመቻቹ አረጋግጠዋል።
በተመሳሳይ ሀገርን ለመታደግ በኅልውና ትግል ለተሰዋው መቶ አለቃ ጌታቸው ሞረዳ ልጅ አባቢያ (ቢኒያም) የአማራ ባለሃብቶች ሕብረት የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
