በህልውና ዘመቻው መስዋእትነት ለከፈሉና አኩሪ ገድል ለፈፀሙ ጀግኖችና ቤተሰቦች እውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥ የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

151

ደሴ፡ ጥር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራን ህዝብ ለማዋረድና አንገት ለማስደፋት የመጣውን የትግራይ ወራሪ ቡድን በመደምሰስ የደቡብ ወሎ ዞን ህዝብና የፀጥታ ኀይሎች መስእዋትነት መክፈላቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን አስታውቀዋል፡፡

በዚህም ለሀገርና ለህዝብ መስዋእትነት ለከፈሉ እና በጦርነቱ አኩሪ ገድል ለፈፀሙ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻ እና ፋኖ ተገቢውን እውቅናና ሽልማት እንደሚሰጥ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

ዞኑ አሁን ላይ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ያደረሰውን ጉዳት በመለየት የመልሶ ግንባታ ስራ እያከናወነ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ በተለይም የፀጥታ ስራውን ትኩረት በመስጠት ሰፊ ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዞኑ የሚገኙ የፀጥታ አካላትን ትጥቅ ለማስፈታት ዞኑ እየሰራ ነው በሚል ከሰሞኑ የሚናፈሰው ወሬ መሰረተ ቢስ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው አቶ አብዱ ሁሴን ተናግረዋል፡፡ ህዝቡ ከጠላት የማረከውን መሳሪያ እንዲታጠቅም ከዚህ ቀደም አቅጣጫ ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ በዚህም ህብረተሰቡ በቂ ስልጠና እንዲወስድ ለማድረግ እየሰራን ነው ብለዋል፡፡

የደቡብ ወሎ ዞን በአሸባሪው ቡድኑ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት እንደደረሰበት የገለፁት አቶ አብዱ ሁሴን ፣ አሁንም ቀሪ የቤት ስራዎች ከፊታችን ይጠብቁናል፤ ወጣቶችም የሀገር መከላከያ ሠራዊትንና የአማራ ልዩ ኀይልን እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ተመስገን አሰፋ–ከደሴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአየር መንገዱ ወደ ጎንደር ዛሬ ባደረገው በረራ ክብረ ወሰን መመዝገቡን ገለጸ።
Next article❝እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)