
ጥር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ወደ ሀገር ቤት ዘመቻ አካል የሆነው የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ግብዣ ትናንት ተካሂዷል፡፡
በመርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው ለመጡ ዳያስፖራዎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፥ ሀገራቸውን ተዘዋውረው እንዲመለከቱም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከልማት ጋር በተያያዘ ባነሱት ሐሳብ፥ ያልታዩ ፕሮጀክቶችን እንዲመለከቱ በማበረታታት ይህም ተጨማሪ ሐሳብ አመንጭተው የተሻለ ሥራ ለመሥራት እንደሚያስችላቸው አንስተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
መንግሥት ምንም አይነት ውሳኔዎችን ሲወስን ሦስት መሰረታዊ ጉዳዮችን አስቀድሞ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ እነሱም ሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ ጥቅምና ሀገራዊ ክብር እንደሆኑ አንስተዋል።
“በመነጋገር እናምናለን” ስንል ቅድመ ሁኔታን ከማስቀመጥ በፊት የሚሉትን መስማት ይቀድማል በማለት እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡
ማንኛውንም ሐሳብ እንሰማለን የማይጠቅመንን እንተዋለን ወደ መስማማት የምንመጣበትን ትክክለኛ የዴሞክራሲ አካሄድ እንከተላለንም ብለዋል፡፡
ሀገርን ማቅናት የምንችለው ሰላምን የምናስፍነው በሰከነ መንገድ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ምንጊዜም ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያውያን የሚሻለውን በጋራ እንወስናለን ነው ያሉት።
የምንወስናቸው ውሳኔዎች ኢትዮጵያን ያስቀደመ በመሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊረዳ ይገባልም ነው ያሉት፥ ይቅርታ ነገን ለማቅናት እንጂ ትናንትን ለመቀየር እንዳልሆነ ሁሉም ሊገነዘብ እንደሚገባ በማንሳት።
ጠላት ብለን የፈረጅነው ሀገር የለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፥ ሆኖም ግን ፖሊሲዎቻቸው ካስቀመጥናቸው መመዘኛዎች አንጻር የማይስማሙ አንዳንድ ሀገራት አሉ ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያን ታሪክ የሚገነዘቡ፣ ኢትዮጵያን የሚያከብሩ እና የወደፊት ተስፋዋን የሚገነዘቡ ሀገራት እንዳሉም ጠቅሰዋል፡፡
“ከእኛ ጋር ሐሳባቸው የሚስማማ ሀገራትን እናጸናለን ፤ ከእኛ ጋር ሐሳባቸው የማይስማማ ሀገራትን ደግሞ መሳሳታቸውን፣ ነጻ የነበርንና ነጻ ሆነን የምንቀጥል እና ምንም ድሃ ብንሆን በክብራችን የማንደራደር ሀገር መሆናችንን ማወቅ አለባችሁ እያልን ወደ እኛ ሐሳብ እናቀርባቸዋለን” ብለዋል፡፡
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/
