
ሁመራ: ጥር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ለ10ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የልዩ ኃይል አባላት ዛሬ በባዕከር የልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት አስመርቋል። የልዩ ኃይል አባላቱ የተገኘውን ወታደራዊ ድል ወደ ላቀ እና ዘላቂ አሸናፊነት ለማሸጋገር ያስችላሉ ተብሏል።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) እንደተናገሩት ባዕከር እና አካባቢው ለዘመናት በወራሪው እና አሸባሪው የትግራይ ቡድን መከራን አሳልፏል።
❝ለአማራ ሕዝብ ነፃነት እና እኩልነት ወንድሞቻችን መራር መስዋእትነት ከፍለዋል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በመስዋእትነት የተገኘውንን ድል ማስቀጠል በእናንተ በዛሬ ተመራቂዎች ያረፈ ነው❞ ብለዋል።

❝የታሪክ አጋጣሚ ሆኖ እናንተ ወታደራዊ ሥልጠና የወሰዳችሁበት ቦታ የአማራ ሕዝብ የእምቢተኝነት ማዕከል ነውና እናንተም ለሕዝባችሁ ነፃነት እምቢ እንደምትሉ አንጠራጠርም❞ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በመልዕክታቸው።
ጦርነቱ አልተጠናቀቀም፤ የአማራ እና የኢትዮጵያ ሕዝብ የኅልውና ስጋቶች ፊት ለፊታችን አሉ ነው ያሉት ርእስ መሥተዳድሩ የአባቶቻችሁ ልጆች ናችሁና ጊዜያዊ ፈተናዎችን ሁሉ ተቋቁማችሁ እንደምታሸነፉ አንጠራጠርም ነው ያሉት።
መንግሥት፣ ባለሃብቱ እና ኢትዮጽያዊያን ሁሉ ከጎናቸው እንደሚቆሙ አረጋግጠውላቸዋል።
ሰልጣኞች አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ስልጠናቸውን በብቃት እንዲያጠናቅቁ ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ የክልሉ መንግሥት እውቅና እና ምስጋና እንዳለው ርእስ መስተዳድሩ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ ለተመራቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት “ለሰንደቅ ዓላማ ልዕልና፣ ለሕዝብ ነፃነት እና ክብር ውድ የሕይዎት መስዋእትነት እና ጀብዱ በሚሠራበት የውትድርና ሙያ ስለተቀላቀላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል። ወታደራዊ ሥነ ምግባር፣ ሕዝባዊ ወገንተኝነት እና የላቀ ግዳጅ አፈፃጸም ይጠበቅባችኋል ብለዋል ኮሚሽነሩ።
ባለፉት ጊዜያት ከሕግ ማስከበር እስከ ኅልውና ዘመቻዎች የአማራ ልዩ ኃይል በላቀ ጀብዱ ሕዝባዊ ዘብነቱን አስመስክሯል ያሉት ኮሚሽነር ተኮላ የዛሬ ተመራቂዎች እስካሁን የተገኘውን ወታደራዊ ድል እና የኢትዮጵያ አሸናፊነት ወደ ላቀ እና ዘላቂ አሸናፊነት እንደምታደርሱት እምነት አለን ብለዋል።
ዘጋቢ፦ ታዘብ አራጋው -ከባዕከር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/
