በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቴክሳስ እና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት የዳላስ ቤተክሕነት ጽሕፈት ቤት የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

213

ባሕር ዳር፡ ጥር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቴክሳስ እና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት የዳላስ ቤተክሕነት ጽሕፈት ቤት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች እና ለሐይቅ ሆስፒታል የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ቤተክሕነት ጽሕፈት ቤቱ ከምእመናን ያሰባሰበውን 1 ሚሊዮን ብር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ውድመት እና ዘረፋ ለደረሰበት በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ ለሚገኘው ሐይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ድጋፍ አደርጓል፡፡ 1 ሚሊዮን ብር ደግሞ በወረራው ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ነው ድጋፍ የተደረገው፡፡
ለሆስፒታሉ የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ እንደገለፁት የሐይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከባድ መሣሪያ ጭምር በመደብደብ ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል፤ የተደረገው ድጋፍም ሆስፒታሉን ለማቋቋም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሽብር ቡድኑ ወረራ በተያዙ አካባቢዎች ጭምር ከሕዝቡ ጎን በመሆን ትልቅ እገዛ ማድረጓን ኀላፊው አንስተዋል፡፡ ወራሪ ቡድኑ የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ ዝርፊያ እና ውድመት ማድረሱንም ጠቅሰዋል፡፡
ዶክተር መልካሙ ከደረሰው ጉዳት በፍጥነት ለማገገም የሁሉንም ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።
ለተፈናቃዮች የተደረገውን ድጋፍ የተረከቡት የአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘላለም ልጅዓለም እንደገለፁት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎችን አፈናቅሏል፤ ግድያ ፈጽሟል፤ ሃብት ንብረታቸውንም ዘርፏል።
ቤተ ክሕነቱ ያደረገው ድጋፍ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚያግዝ ነው፤ ኮሚሽኑም በአግባቡ ያደርሳል ነው ያሉት። ለተደረገው ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል። ሌሎች አካላትም ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
በአሜሪካን ሀገር የቴክሳስና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ንጹሐን ዜጎች የጉዳቱ ሰለባ ሆነዋል፤ ጉዳት ከደረሰ በኋላም ተገኝቶ እገዛ ማድርግ መልካም ነው ብለዋል። የተደረገው ድጋፍ በቂ አይሆንም ያሉት ብፁዕነታቸው ድጋፉ ቤተክርስቲያን ሁሉን አቃፊ፣ ተምሳሌት እና የሁሉም እናት መሆኗን ማሳያ ነው ብለዋል። ተፈናቃዮቹ በዘላቂነት እስኪቋቋሙ ድጋፍ እንደሚደረግም አስታውቀዋል፡፡
ዘጋቢ፦አዳሙ ሽባባው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከኢፌዴሪ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የተሰጠ መግለጫ።
Next article❝ለአማራ ሕዝብ ነፃነት እና እኩልነት ወንድሞቻችን መራር መስዋእትነት ከፍለዋል፤ በመስዋእትነት የተገኘውንን ድል ማስቀጠል በእናንተ በዛሬ ተመራቂዎች ያረፈ ነው❞ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)