
ባሕር ዳር፡ ጥር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሊንክ ኢትዮጵያ የተሰኘ እና በትምሕርት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአማራ ክልል በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተጎዱ ትምሕርት ቤቶች ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምሕርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድርጅቱ ድጋፉን ለአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ አስረክቧል፡፡
አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በአማራ ክልል በፈፀመው ወረራ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አውድሟል፤ ዘርፏል። ወረራ በተፈፀመባቸው አካባቢዎች በእጅጉ ከተጎዱ ተቋማት መካከል የትምሕርት ተቋማት ከግንባር ቀደሞቹ ናቸው።
አሸባሪው ቡድን በወገን ጦር ተቀጥቅጦ ከወጣ በኋላ ተቋማትን መልሶ ለማቋቋም ጥረቶች እየተደረጉ ነው። የክልሉ መንግሥትም የሽብር ቡድኑ ያወደማቸውን ተቋማት መልሶ ለማቋቋም ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። በተደረገው ጥሪ መሠረት መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ድጋፍ እያደረጉ ነው።
ሊንክ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምሕርት ተቋማት ማገዝ የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ አስረክቧል። ድጋፉ የተደረገው በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስተባባሪነት መሆኑንም ታውቋል።
ድጋፉን ያስረከቡት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ንብረት አስተዳዳር ዳይሬክተር ኃይለማርያም አየለ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ተቋማትን በማስተባበር ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች የሚውል ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሊንክ ኢትዮጵያ የተሰኘውን ግብረ ሰናይ ድርጅትም በማስተባበር ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የትምሕርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት። ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥም ገልፀዋል። ለወገን ደራሽ መሆናችንን እያስመሰከርን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር ካሳ አባተ በጦርነቱ ምክንያት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ገልፀዋል። ተማሪዎችን ወደ ትምሕርት ቤት ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ተቋማት ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሊንክ ኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ በአስቸኳይ የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። ሌሎች ተቋማትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው የጠየቁት። በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አስተባባሪነት በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የምግብ ድጋፍ መድረጉም በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
