“የጥምቀት በዓልን ስናከብር በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱትን በመደገፍ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በማቋቋምና ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት በመገንባት ሊሆን ይገባል”ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል

163

ጎንደር፡ ጥር 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ለጥምቀት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
ብፁዕነታቸው ጥምቀት የመንግሥተ ሰማያት በር፤የሐጢያት ሥርየት የተገኘበት፤ ዳግም ልደትና አዲስ ህይወት የምናገኝበት ነው ብለዋል።
በዓሉን ለማክበር የመንግሥትን ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ ሀገር ቤት የገባችሁ ኹሉ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል በመልእክታቸው።
የጥምቀት በዓልን ስናከብር በጦርነቱ ምክንያት የተጎዱትን በመደገፍ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በማቋቋምና ጉዳት የደረሰባቸውን ተቋማት በመገንባት ሊሆን እንደሚገባም አሳስበዋል።
ሰላም ከሌለ ምንም የለም ያሉት ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ክብረ በዓሉን ስናከብር የሰላምን ዋጋ በመገንዘብ በአንድነትና በመከባበር ልናከብር ይገባልም ብለዋል።
ምዕመናን ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በመከተል ተቦታትን እንዲያጅቡ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡- ስማቸው እሸቴ – ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበበርሃዋ ገነት የደመቁት እነሞት አይፈሬ!
Next articleሊንክ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምሕርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።