“የወልድያ ዩኒቨርሲቲን በማቋቋም ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነው” የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት

137

ባሕር ዳር፡ ጥር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሸባሪው ህወሃት ጉዳት የደረሰበትን ወልድያ ዩኒቨርሲቲ መልሶ በማቋቋም የመማር ማስተማሩን ስራ ለማስጀመር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር አበበ ግርማ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲው በአፍሪካ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ተወዳዳሪ እንዲሆን ተደርጎ የተደራጀ እንደነበር የገለጹት ዶክተር አበበ፤ አሸባሪው ቡድን ወረራ በፈፀመበት ወቅት ዩኒቨርሲቲው ላይ የከፋ ጉዳት ማድረሱን አስታውሰዋል።

ቡድኑ የዩኒቨርሲቲውን ልዩ ልዩ ንብረት የሚችለውን ዘርፎ፣ ያልቻለውንም ደግሞ አውድሞ አገልግሎት እንዳይሰጥ ማድረጉን ገልጸዋል።

በዘመናዊ መንገድ የተደራጀውን ላብራቶሪ፣ ቤተ መጽሐፍት፣ አይሲቲ፣ የመምህራንና የተማሪዎች መኖሪያ፣ መማሪያና መመገቢያ ህንፃዎች ጉዳት ካደረሰባቸው መካከል መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ማሽኖች፣ የመብራት፣ የውኃና ሌሎችን የተቋሙን ንብረቶችን በማውደም በታሪክ የማይረሳ ጥቁር ጠባሳ የጣለ ነው ብለዋል ዶክተር አበበ፡፡

በደረሰው ውድመት የተነሳ መምህራንና ተማሪዎች በተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የመማር ማስተማር ስራ እንዲቀጥሉ ጊዜያዊ መፍትሄ መሰጠቱን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲውን መልሶ ስራ ለማስጀመር መንግስትና አጋር አካላት ጠንካራ ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችም አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲሰጡ ተመድበው ማገዝ ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት መደረጉን አመልክተዋል።

በዚህም እስከ የካቲት ወር 2014 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊው ማስተካከያ ተደርጎለት መልሶ በማቋቋም የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር በቅንጅት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በመጀመሪያው ዙርም ተመራቂና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መቀበል የሚያስችል ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ዶክተር አበበ አስታውቀዋል፡፡

ለዚህም ቅድሚያ የሚሰጣቸው ጉዳዮች ተለይተው እየተስተካከሉ መሆኑን ጠቁመው፤ የተማሪዎች ማደሪያና መማሪያ ክፍሎች፣ መመገቢያ አዳራሽና ቁሳቁስ፣ ውኃ፣ መብራትና ሌሎች መሰረተ ልማቶችም እየተጠገኑ መሆኑን ነው ያመለከቱት።

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚያስተምራቸው ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች እንደነበሩት የዘገበው ኢዜአ ነው፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሸባሪው ትሕነግ በአፋር የዘር ማጥፋት እየፈፀመ መሆኑን ክልሉ አስታወቀ።
Next articleወልቃይት ጀግኖቿን አመሰገነች።