አሸባሪው ትሕነግ በአፋር የዘር ማጥፋት እየፈፀመ መሆኑን ክልሉ አስታወቀ።

171

ጎንደር፡ ጥር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትሕነግ በአፋር አብአላ በኩል በከፈተው ግንባር በንፁሃን ላይ ድጋሚ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ እየፈፀመ መሆኑን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ፡፡

የሽብር ቡድኑ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በአስቸኳይ መቆም አለበት ሲል መግለጫ ያወጣው የክልሉ መንግሥት በኪልበቲ ረሱ (ዞን ሁለት) አብአላ በኩል በከፈተው አዲስ ግንባር በተከታታይ እየተኮሰ ባለው ከባድ መሳሪያ ንፁሃን ዜጎችን መጨፍጨፉን ቀጥሏል ብሏል።

በዚህም ጋሊኮማን ጨምሮ በአራት ዞኖች ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎች ያደረሰውን የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ በድጋሚ በአብአላና በመጋሌ እየደገመ ይገኛል ተብሏል።

ቡድኑ በከባድ መሳሪያ በታገዘ ድብደባው በርካታ ንፁሃን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፣ በበርካታ ሺሕዎች የሚቆጠሩ ደግሞ በጥቃቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለስደት ተዳርገዋል ነው ያለው።

የትግራይን ሕዝብ ከሁሉም ኢትዮጵያዊያን ጋር ለማናከስ ቆርጦ የተነሳው አሸባሪው ትሕነግ የአፋርና ትግራይ ሕዝብን በማናከስ እድሜውን ለማራዘም እየጣረ ነው ብሏል፡፡

ቡድኑ ዳግም ወረራ ለማካሄድ ጥረት እደረገ መሆኑን ያሳወቀው የአፋር ክልል ትናንትና ዛሬም በተለያየ መልኩ ተደራጅቶ በመምጣትና ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ንፁሃንን መግደሉንና ንብረት ማውደሙን ገልጿል፡፡

የምድር ድሮኖቹ አሁንም ቢሆን የሽብር ቡድኑን በሚገባው ቋንቋ እያናገሩት ነው፤ ወደ አፋር ክልል ዘልቆ እንዳይገባም ብርቱ ተጋድሎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ቡድኑ ከጥፋት መንገዱ አለመታቀቡንና በአፋር በኩል እየፈፀመ ባለው የንፁሃን ጭፍጨፋ ምክንያት ጦርነቱ አለመቆሙን አሳውቋል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“አባቴ አደራ የሰጠኝ ቤተሰቦቼን ሳይሆን ኢትዮጵያንና ሰንደቅ ዓላማዋን ነው” ምክትል መቶ አለቃ ሕይወት ዐብይ
Next article“የወልድያ ዩኒቨርሲቲን በማቋቋም ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነው” የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት