
ጎንደር፡ ጥር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገር ከገጠማት አደጋ ለመታደግ የጋራ ምክክሩ እጅግ ጠቃሚ እና አስፈላጊ መፍትሔ መሆኑን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ አመለከቱ።
አቶ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፣ ሀገሪቱ በይደር በመጡት ችግሮች እና የተለያየ ፍላጎቶች፣ አመለካከቶች እና ዋልታ ረገጥ ጥያቄ ባላቸው የፖለቲካ ኃይሎች ተወጥራ ሀገረ መንግሥቱ እና የሀገሪቱ ኅልውና ጥያቄ ውስጥ ከገባ ውሎ አድሯል።
የተለያዩ አመለካከቶች እና ጥያቄዎችም እንደ ውበት ተቆጥረው ለውይይት በር ከፋች መሆን ሲገባቸው አልፈው ለዜጎች ሞት እና ስቃይ እንዲሁም የጦርነት መነሻ ሆነዋል።
አመለካከቶቻችን እና ጥያቄዎቻችን ወደ ውይይት ቢመጡ ኖሮ ይህ ሁሉ የሰው ሕይወት መጥፋት እና ንብረት ወድመት ባልተከሰተ ነበር ያሉት አቶ ክርስቲያን፣ ነገር ግን ሀገሪቱን ለመታደግ ሊደረግ የታቀደው ምክክር ሚናው የላቀ ቢሆንም “ኢትዮጵያ በመቃብሬ ላይ ነው፤ ሲኦልም ቢሆን ወርጄ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ” ከሚል አሸባሪ ቡድን ጋር ግን ፈጽሞ መካሄድ እንደሌለበት ጠቁመዋል።
ብሔራዊ ምክክሩ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቅቡልነት ያለው ጉዳይ ከመሆኑም በላይ በምክክሩ የሚነሱ ሐሳቦች ለሀገሪቱ መፃዒ ዕድል ወሳኝ ነው፤ ለዘላቂ መተማመን እና መከባበር በብሔራዊ ምክክሩ በይቅርታ የሚታለፉ ጉዳዮች በይቅርታ በማለፍ በይቅርታ የማይታለፉ ጉዳዮችን ደግሞ ተበዳዮች የሚካሱበት እና በዳዮች በፍትሕ ሽግግር የሚዳኙበት ሁኔታ ይፈጠራል ብለዋል።
በምክክሩ ለዘመናት የዘለቁ ችግሮች የተሟላ እልባት ያገኛሉ ማለት ሳይሆን በዋናነት ለሀገረ መንግሥቱ ለኅልውና አደጋ የሆኑ፣ የሕዝቡ አብሮነት፣ ሰላም እና አንድነት ጥያቄ ውስጥ ያስገቡ ጉዳዮች የትኩረት አጀንዳ እንደሚሆኑ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ከሁሉም በላይ የምክክሩን አቅጣጫ ለማሳት እና ወዳልተፈለገ መንገድ ለመምራት የሚፈልጉ ወገኖች አካሄዳቸውን ማስተካከል እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
