በአፋር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የመድሐኒትና የሕክምና መሳሪያ ድጋፍ ተደረገ፡፡

84

ባሕር ዳር፡ ጥር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያና የኢትዮጵያ ጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማኅበር በአፋር ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው ጤና ተቋማትን ሥራ ለማስጀመር እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ ከ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የሕክምና መሳሪያዎችና መድሐኒቶች ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉን የተረከቡት የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አቶ ያሲን ሃቢብ እንደገለጹት በክልሉ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ የጤና መሠረተ ልማቶችን መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።
“የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያና የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማኅበር ያደረጉት ድጋፍ በአሸባሪው ጉዳት የደረሰባቸው ጤና ተቋማትን ወደ ሥራ ለማስገባት እየተደረገ ላለው ጥረት አቅም ይሆናል” ብለዋል።

አቶ ያሲን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የሐረሪ ክልል ተቋማቱን ወደ ሥራ ለማስገባት ትልቁን ድርሻ ወስደው ድጋፍ ማድረጋቸውንም አንስተዋል። ሌሎች መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አጋር አካላትም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆኑን ነው የተናገሩት።
ለተደረገው የመድሐኒትና የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በክልሉ መንግሥትና በተጎጂዎች ስም አመስግነው ዳያስፖራውና የተራድኦ ድርጅቶችም ለተጎጂዎች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ሃብቴ ድርጅቱ ከዚህ በፊት ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስና መድሐኒት መደገፉን አስታውሰዋል። ዛሬም ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ የተለያዩ መድሐኒቶችን ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው “ድርጅቱ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል” ብለዋል።

ሌላው ድጋፍ ያደረገው የኢትዮጵያ ጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ዘነበ አካሉ በበኩላቸው የሙያ ማኅበሩ የተለያዩ መድሐኒትና ለማዋለጃ አገልግሎት የሚውሉ የሕክምና ቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
ማኅበሩ ያደረገው ድጋፍ ከ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ተናግረዋል።
በቀጣይም የክልሉን ክፍተት መሰረት በማድረግ ማኅበሩ መድሐኒትና ተያያዥ የሕክምና ግብአቶችን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል ሲል የዘገበው ኢዜአ ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የታፈኑ እውነታዎች” የተሰኘው መጽሐፍ ምረቃ በጎንደር ከተማ እየተካሔደ ነው።
Next article“ብሔራዊ ምክክሩ ሀገር ለመታደግ ቁልፍ መፍትሔ ነው” አቶ ክርስቲያን ታደለ