
ጎንደር፡ ጥር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መጽሐፉ ዐማራ በኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ያበረከተውን አበርክቶ በውስን አምድ ደረጃ ከታሪክ አውድ አኳያ ሰፊ ትንታኔ ሰጥቷል። ከፍጥረቱ ጀምሮ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ ሆኖ የተመሰረተው ትህነግ በዐማራ ሕዝብ ላይ የፈጠረውን የተዛባ ትርክት በታሪክ ማስረጃዎች ዋጋ ለማሳጣት አጋዥ ነው ተብሏል።
ከ1983 ዓ.ም በፊት ወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የስሜን በጌምድር ጠቅላይ ግዛት አካል መሆናቸውን በሚያረጋገጡ ሰነዶች በመመስረት ትንታኔ ተደርጎበታል።
ትህነግ በትረ-ሥልጣኑን ከተቆጣጠረ በኋላ በወልቃት፣ ጠገዴና ጠለምት በባሕልና በማንነት እንዲሁም በኢኮኖሚ ላይ ያደረሰውን ምዝበራና ጥፋት፤ ትህነግ ከምስረታው ጀምሮ በጫካ፣ በአገዛዝና በአሸባሪነት ዘመኑ በሕዝብ እና በሀገር ላይ የፈፀማቸውን ዋና ዋና ክህደቶች አጉልቶም አውጥቷል።
ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም የተጀመረውን ሕግ የማስከበር ዘመቻ ተከትሎ ነጻ በወጡት ወልቃይት፣ጠገዴና ጠለምት የድኅረ-ነጻነት ሁኔታዎች ምን እንደሚመስሉ እውነታዎችን
ለማሳወቅና በቀጣይ በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ጉዳይ መሆን ስላለባቸው የሕግ፣ የፖለቲካና የማኅበራዊ ውል መፍትሔዎች ዙሪያ ምክረ-ሐሳቦች በመጽሐፉ ተመላክተዋል።

በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ሰብሳቢ ታፈረ መላኩ (ዶ.ር) መጽሐፉ አሸባሪው ትህነግ ከጫካ ምስረታው ጀምሮ እስካሁን ድረስ በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ግፍ በተደራጀ መልኩ ለማመላከት አጋዥ ይሆናል ብለዋል።
በቀጣይም በራያ የፈጸመውን ጭቆናና ብዝበዛን የሚያሳይ በጥናት ላይ የተመሰረተ መጽሐፍ ለማሳተም በሒደት ላይ ነን ብለዋል።
“የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የታፈኑ እውነታዎች” የተሰኘው መጽሐፍ በስድስት ከፍተኛ ባለሙያዎች ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።
በመጽሐፉ ምረቃ ወቅት ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ምሁራንና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ስማቸው እሸቴ -ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/
