በፋሲል ከነማ ሰፖርት ክለብ የተዘጋጀ የ5 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ በጎንደር ተካሄደ።

178

ጎንደር፡ ጥር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “ለአሸናፊዎች እሮጣለሁ” በሚል መሪ ሐሳብ በፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ የተዘጋጀ የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድር በጎንደር ተካሂዷል።

ውድድሩ የተዘጋጀው ክለቡ በየዓመቱ በጥምቀት ሳምንት የሚያዘጋጀው የገቢ ማሰባሰቢያ መሆኑ ተገልጿል።

ውድድሩ መነሻውን ማራኪ በማድረግ በመስቀል አደባባይ የተፈፀመ ሲሆን ከ10 ሺህ በላይ ሰዎች መሳተፋቸውን የክለቡ ደጋፊዎች ማኅበር ፕሬዚዳንት አቶ ደመላሽ አበበ ገልጸዋል።

ባሳለፍነው ዓመት ክለቡ ያስመዘገበውን ድል እና ሀገሪቱ የገጠማትን ወራሪ ድል ማድረጓን ለመዘከር መሪ ቃሉን “ለአሸናፊዎች እሮጣለሁ” በተባለው የጎዳና ላይ ሩጫ በአዋቂ ወንዶች እና ሴቶች እንዲሁም በታዳጊ ሴቶች እና ወንዶች አሸናፊዎች የተሸለሙበት ነው።

እንዲህ ዓይነት ውድድሮች በዓሉን ከማድመቅ ያለፈ ስፖርታዊ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ተወዳዳሪዎች ተናግረዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article“ሕዝቡ ሁልጊዜ ዝግጁ ሆኖ ሀገሩን መጠበቅ ይኖርበታል” አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ
Next article“የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የታፈኑ እውነታዎች” የተሰኘው መጽሐፍ ምረቃ በጎንደር ከተማ እየተካሔደ ነው።