
ጎንደር፡ ጥር 08/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
በኢትዮጵያ ልጆች በተባበረ ክንድ በግንባር ጦርነት የተዋረዱት እና የተቀጡት አሸባሪ ቡድኖች ከበስተጀርባ የኢትዮጵያን ሰላም እና ልማት ለማደናቀፍ መጣራቸው ስለማይቀር ሕዝቡ ሁልጊዜ ዝግጁ ሆኖ ሀገሩን መጠበቅ እንደሚኖርበት አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ ጥሪ አቅርቧል።
በዓለም አደባባይ፤ በግንባር እና በተለያዩ ዘመቻዎች ኢትዮጵያ ላይ ጦርነት ቢከፈትም ኢትዮጵያ በልጆቿ የተባበረ ክንድ ጦርነት ጎሳሚዎቹ ተዋርደው ተደምስሰዋል ብሏል አትሌት ኃይሌ።
በጦርነት የተዋረዱት እና የተቀጡት አሸባሪ ቡድኖች እና አንዳንድ ምዕራባውያን መንግሥታት፣ የእነ ግብፅን እና የራሳቸው ተከታዮች ለመጥቀም እንዲሁም የአሜሪካ አስተዳደር የራሱን ጥቅም እና ፍላጎት በአፍሪካ ምድር ለማስከበር ሲሉ የማያደርጉት ነገር በምድር ላይ የለም ሲልም ተናግሯል።
ጦርነቱ አብቅቷል ብለን ተዘናግተን መቀመጥ የለብንም ያለው አትሌት ኃይሌ፣ ከጦርነቱ በስተጀርባ የሚጠብቁን ዓይነተ ብዙ ውስብስብ እና ስውር ጦርነቶች አሉብንና ሁሉም ዜጋ በንቃት መሥራት መቻል አለበት ሲል አሳስቧል።
የከረምንበት ጦርነት በጀመርነው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምክንያት የመጣብን ውርጂብኝ ነው ያለው አትሌት ኃይሌ፣ ጠላቶቻችን አሁንም አርፈው ስለማይተኙልን ሁላችንም ነቅተን አገራችንን መጠበቅ አለብን ብሏል።
አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ በምድራችን የከፋውን ሀገራዊ ስቃይ እያየንበት ያለውን ግድባችንን አጠናቀን የፈሯትን የአፍሪካ ቀንድ ኃያል ሀገር ኢትዮጵያን መመስረት መቻል አለብን ብሏል።
የኢትዮጵያ ኃያል ሀገርነት መቼም የማይቀር ጉዳይ መሆኑን ሁላችንም አውቀን፣ ዛሬ ሕዝብ ሲዋጋ እና ሲዋደቅ በንቃት አብሮ በመታገል ኃያልነቷን ማፋጠን ይገባል ያለው አትሌት ኃይሌ፤ በተቃራኒ ቆሞ ለሚያዩት ነገ በራሳቸው እና በልጆቻቸው ፊት የሀፍረት ካባ ይለብሳሉና ያለምንም መዘናጋት ሁሉም ዜጋ የየድርሻውን ሊያበረክት እንደሚገባ አሳስቧል።
በጦርነት የተጎዱ አባቢዎችን መልሶ በመገንባት፣ በመተባበር እና የድርሻችንን ማበርከት ይገባናል፤ የማንችል እንኳን ቢሆን በተቃራኒው ቆመን እንቅፋት ልንሆን አይገባም ማለቱን ኢፕድ ዘግቧል።
ይህን ካላደረግን ግን በኋላ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል ያለው አትሌት ኃይሌ፤ አሁን ላይ ዜጎች ጠላትን በማስወገድ እና ልማትን በማፋጠን ካልተረባረብን የምናጣው ብዙ መሆኑንም ተናግሯል።
ታግለው፣ ተባብረው ይችን ጊዜውን ያለፉት ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ግን ነገ ዘና ብለውና ብሩኋን የኢትዮጵያን ፀሐይ ሙቀው፣ በዓለም አደባባይ ታውቀው እና ተከብረው አንገታቸውን ቀና አድርገው በኃያሏ ኢትዮጵያ ይኖራሉ ብለዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/
