ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተላለፈ መልዕክት

932

አሸባሪው የትግራ ወራሪ እና ዘራፊ ቡድን አማራ ክልል ላይ ባካሄደው ወረራ በክልላችን ሕዝብ እና መንግሥት ሃብት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እና ውድመት አድርሷል።

የወራሪውን ቡድን ዘረፋ እና ውድመት ተከትሎ ጉዳት የደረሰባቸውን የክልላችን ሕዝቦች ለማቋቋም በሚል የተለያዩ አካላት የድጋፍ ማሰባሰቢያ የሒሳብ ቁጥሮች እና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቶች እያሰናዱ እንደሆነ እየተመለከትን ነው። ነገር ግን ይህ ድርጊት ለቁጥጥር የማይመች እና ከክልሉ መንግሥት እውቅና ውጭ በመሆኑ በዚህ አይነት ድርጊት በመሳተፍ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ የክልሉ መንግሥት ያሳስባል።

በቅርቡም የክልሉ መንግሥት የማቋቋሚያ ገቢ ዝግጅቶች እና የሒሳብ ቁጥሮችን የሚያሳውቅ በመሆኑ ሕዝባችንን መልሶ ለሟቋቋምና ዐሻራችሁን ለማሳረፍ ዝግጅ እንድትሆኑ ጥሪውን ያስተላልፋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች እና በኅልዉና ዘመቻው የተሳተፉ አካላትን መደገፍ የሚያስችል የንግድ እና ባዛር በጎንደር ከተማ ተጀምሯል።
Next articleኑና በጎንደር አንድ ላይ ሆነን ቃል እንሰር!