የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

434

ደሴ፡ ጥር 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል 2 ሚሊዬን ብር የሚያወጣ የእህል ድጋፍ ለደቡብ ወሎ ሀገረስብከት አስረክቧል።

ድጋፉን በደሴ ከተማ በመገኘት ያስረከቡት የቅዱስ ሲኖዶሱ ተወካይ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 400 ኩንታል የፊኖ ዱቄት ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል። ቅዱስ ሲኖዶሱ እንደ ደቡብ ወሎ ሀገረስብከት ሁሉ ተመሳሳይ ድጋፎችን በሰሜን ወሎ እና ዋግኽምራ ዞን ሀገረስብከቶች እንደሚያደረግ ገልጸዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ ድጋፉ ቤተክርስቲያኗ ከተቸገሩ ወገኖች ጎን መቆሟን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

በድጋፍ ርክክቡ ላይ የተገኙት የደሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የማኅበራዊ ጉዳይ አማካሪ አቶ ሰለሞን ጋሻው በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከተማዋ ለችግር የተጋለጡ ወገኖች ቁጥር ከ300 ሺህ በላይ መድረሱን በመጠቆም እነዚህን ወገኖች ለመደገፍ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ፡-ቤተልሔም ሰለሞን-ከደሴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝ዜጎች ከፋፋይ ከሆኑ ሐሰተኛ መረጃዎች ራሳቸውን በመጠበቅ ኢትዮጵያን መገንባት ላይ ትኩረት ማድረግ ይገባቸዋል❞ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ
Next articleከደሴ እስከ ወልድያ ያሉት ከተሞች ኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ።