መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

508

ባሕር ዳር፡ ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታውቋል።

የክልሉ መንግሥት ከፋኖ አደረጃጀት አባላት ጋር ተወያይቷል።

ፋኖ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሀገርና ሕዝብን እየታደገ ያለ መከታ ኃይል ነው። ስለሆነም የፌደራልም ኾነ የክልል መንግሥት ፋኖን ትጥቅ የማስፈታት ሐሳብ የለውም፤ ሊኖረውም አይችልም ተብሏል በመድረኩ።

በቀጣይ የክልሉ መንግሥት የመሳሪያ አስተዳደር ሥርዓቱን ሊያሻሽል እንደሚችልም ተገልጿል።

ፋኖ በስምም ሆነ በግብሩ የአማራ ሕዝብ ክብር መገለጫ በመሆኑ በፋኖ ስም የሚነግዱ አካላትን ፋኖና መንግሥት በጋራ ይታገላሉ ተብሏል። ፋኖን ማደራጀትና ማጠናከር የክልሉ መንግሥት አቅጣጫና ተግባር ኾኖ ሳለ ትጥቅ ማስፈታት የሚለው አሉባልታ አማራን የመከፋፈል እርስ በርስ የማጋጨት የማዳከም ሴራ አካል መሆኑም ተገልጿል።

ዘጋቢ:- አቢዮት ከፋለ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቴክሳስና አካባቢዋ ሀገረስብከት የዳላስ ወረዳ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ድጋፍ አደረገ።
Next articleበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ክፍለ ከተማ አብያተ ክርስቲያናት በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።