በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቴክሳስና አካባቢዋ ሀገረስብከት የዳላስ ወረዳ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ድጋፍ አደረገ።

207

ደብረብርሃን፡ ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቴክሳስና አካባቢዋ ሀገረስብከት የዳላስ ወረዳ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የቴክሳስና አካባቢዋ ሀገሮች ሊቀጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ድጋፉን አስረክበዋል።

በዞኑ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሆንም ጠይቀዋል ብፁዕነታቸው።

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረፃድቅ ለደረሰው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው ሌሎች ወገኖችም ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በደረሰው ጉዳት ማዘናቸውን የገለፁት ብፁዕነታቸው በውጭ የሚኖሩ ምዕመናን ድጋፍ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።

ዘጋቢ:- ኤልያስ ፈጠነ- ከደብረብርሃን

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዳያስፖራዎች ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next articleመንግሥት ፋኖን ትጥቅ ሊያስፈታ ነው የሚለው አሉባልታ መሰረተቢስና የአማራን ሕዝብ ለመከፋፈል የታለመ የጠላት ሴራ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።