ዳያስፖራዎች ለወገን ጦር ድጋፍ አደረጉ፡፡

77

ባሕር ዳር፡ ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎች ለወገን ጦር 500 ሺህ ብር የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ ኑሮአቸውን በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዛት ሳንዲያጎ ከተማ ያደረጉት ኢትዮጵያውያኑ የአልባሳት እና የንፅህና መጠበቂያ ነው ለፀጥታ አካላት ድጋፍ ያደረጉት፡፡

ድጋፉን በአካል በመገኘት ያስረከቡት ክንፈገብርኤል አበራ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ቀደም በደቡብ ወሎ ዞን ሐይቅ ከተማ በአሸባሪው የትግራይ ቡድን ለወደመው ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል፡፡

ሌላኛው በሳንዲያጎ ከተማ የሚኖሩት ዓለማየሁ ስዩም ወደፊት በረጅም ጊዜ ዕቅድ ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን መገንባት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት ዋና ሳጅን ሳምሶን ጌጡ የተደረገው ድጋፍ ለሀገርና ሕዝብ ሲሉ ጀብድ እየሠሩ ላሉ የፀጥታ አባላት ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ወደፊትም ተመሳሳይ ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ዋና ሳጅን ሳምሶን ጌጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ኪሩቤል ተሾመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleነዋሪነታቸው በኖርዌይ የሆነው ኢትዮጵያዊ አስማማው ተሻማው በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት ለደረሰበት አሚኮ የካሜራ ድጋፍ አደረጉ፡፡
Next articleበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቴክሳስና አካባቢዋ ሀገረስብከት የዳላስ ወረዳ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ድጋፍ አደረገ።