‹‹ሀገራዊ ምርጫና የምርጫ ባለድርሻ አካላት ሚና ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ›› በሚል ርዕስ አዲስ አበባ ላይ ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡

212

ባሕር ዳር፡ መስከረም 27/2012 ዓ/ም (አብመድ) በተያዘው ዓመት ለማካሄድ በታቀደው ምርጫ ላይ እየተካሄደ በሚገኘው ምክክር ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የብዙኃን መገናኛ ተቋማትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት እየተሳተፉ ነው፡፡

ተዓማኒ የምርጫ አስተዳደር መገንባት፣ በኅብረ ብሔራዊ ማኅበረሰብ ውስጥ ተዓማኒ ምርጫ ማድረግ፣ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አባል ማሻሻያና የምርጫ ዝግጅት፣ በምርጫ ሂደት ውስጥ ተዓማኒነትን መገንባትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ትብብር መፍጠር፣ በአዲሱ የምርጫ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉ የመንግሥት ግዴታና የፖለቲካ ፖርቲዎች መብት የሚሉ ጭብጦች ላይ ነው ምክክር የሚደረገው፡፡

የምርጫ ሁከት ጥናትና የቅድመ ሁከት ማሳዎቂያ ዘዴዎች ለኢትዮጵያ፣ በመጭው ምርጫ ወቅት ሠላምና ደኅንነትን ለማረጋገጥ መወሰድ ያለባቸዉ ሁኔታዎች የሚሉ ጉዳዮች ላይም ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡ ምክክሩ ለሁለት ቀናት የሚካሄድ ነው፡፡

ዘጋቢ፡- አዱኛ ዓለምጸጋ

Previous articleበቅማንት የማንነትና የራስ አስተዳደር ጥያቄ ዙሪያ አዲስ አበባ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
Next article‹‹በሕገ-ወጥ ደላሎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል፡፡›› ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር