
ወልድያ፡ ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ከከተማው ነዋሪዎች፣ ከንግዱ ማኅበረሰብ፣ ከባለሃብቶች እና ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ያሰባሰበውን ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ምግብና የተለያዩ አልባሳት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተፈናቀሉ እና ሃብት እና ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች ድጋፍ አድርጓል፡፡
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ በትግሉ ተስፋሁን የባሕር ዳር ከተማ ማኅበረሰብ በኅልውና ዘመቻው ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን ጠቅሰዋል።
ዛሬ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚሆን የምግብ እና የአልባሳት ድጋፍ መደረጉን የገለጹት ኀላፊው መልሶ በማቋቋምና በመገንባት ሂደት ከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የትምህርት መምሪያ ኀላፊ ጋሻው አስማሜ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
በዞኑ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምህርት፣ የጤና እና ሌሎች ማኅበራዊ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እና ወደ ሥራ ለማስገባት ኢትዮጵያዊያን ድጋፍ እንድያደርጉ ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፡- ባለ ዓለምየ-ከወልድያ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/