
ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚቴ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በአስቸኳይ ጊዜ የድጋፍ አሰጣጥ ሂደት አስፈፃሚ አካላት ያሳዩት ፈጣን ምላሽ እና ቅንጅታዊ አመራር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የብሔራዊ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በስብሰባው ላይ እንደተናገሩት፤ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በሚስተዋለው የድርቅ አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ፈጣን የድጋፍ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል፡፡
ቀደም ባሉት ጊዜያት በአስቸኳይ ጊዜ የድጋፍ አሰጣጥ ሂደት አስፈፃሚ አካላት ካሳዩት የተቀናጀ ርብርብ በተሻለ ትኩረት የድርቅ አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ፈጣን የድጋፍ ምላሽ ሊያገኙ እንደሚገባ አቶ ደመቀ አሳስበዋል፡፡
ብሔራዊ ኮሚቴው ባስቀመጠው አቅጣጫ በአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አቅርቦት እና ሥርጭት ሂደት ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ዘላቂ በሆነ መልኩ በመፍታት የድጋፍ ምላሹ የመጨረሻ ተጠቃሚዎችን ማዕከል ማድረግ እንደሚገባው አቶ ደመቀ ገልጸዋል፡፡
ሀገሪቱ የገጠማትን የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች ተቋቁማ እንድትሻገር የዳያስፖራው ማኅበረሰብ ላደረገው ድጋፍ አቶ ደመቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በቀጣይም በሁሉም አቅጣጫ የተጀመረው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የብሔራዊ አደጋ መከላከል ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ በበኩላቸው፤ ብሔራዊ ኮሚቴው በሚያሳልፋቸው ውሳኔዎች እና በሚያስቀምጣቸው አቅጣጫዎች መሰረት የተጀመሩት የድጋፍ እና ምላሽ አሰጣጥ ሥራዎች በሚታይ መልኩ ወደ መሬት መውረድ ጀምረዋል፡፡
ይሁንና ሀገሪቱ ከገጠማት ውስብስብ ችግሮች አኳያ ከአጋር አካላት የሚደረገው ድጋፍ በቂ በሚባል ደረጃ ባለመሆኑ ምክንያት ጅምር የድጋፍ እና ምላሽ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ አሉታዊ ጫና እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
የብሔራዊ አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ኮሚቴ በአስቸኳይ ጊዜ የድጋፍ አሰጣጥ ሂደት አስፈፃሚ አካላት ያሳዩት ፈጣን ምላሽ እና ቅንጅታዊ አመራር ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ ማስተላለፉን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/