የከተማና መሠረተልማት ሚኒስቴር ለአማራ ክልል 150 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

167

ባሕር ዳር: ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በአማራ ክልል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተጎዱ ወገኖች የሚውል 150 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የትግራይ አሸባሪና ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል ባደረገው ወረራ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን አፈናቅሏል፣ ብዙዎችን በግፍ ገድሏል፣ ሀብትና ንብረታቸውን ዘርፏል፣ አውድሟል። የሽብር ቡድኑ በወገን ጦር ተቀጥቅጦ ከወጣ በኋላ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። የመንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትና ባለሀብቶች ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እያደረጉ ነው። የተፈናቀሉ ወገኖችም ወደቀያቸው እየተመለሱ ነው።

የከተማና መሠረተልማት ሚኒስቴር በአማራ ክልል ለተጎዱ ወገኖች ማቋቋሚያ የሚውል ድጋፍ አድርጓል። ድጋፉን ያስረከቡት የከተማና መሠረተልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ጠላቶቻችን ባሰቡልን ሳይሆን በድል ስለተገናኘን እንኳን ደስ ያለን ብለዋል። የሽብር ቡድኑ የገጠመው ከመላው ኢትዮጵያውያን ጋር ነው ያሉት ሚኒስትሯ የሽብር ቡድኑ ከዓመታት በፊት ጦርነት እንደጀመረም አስታውሰዋል። የሽብር ቡድኑን በአንድነት ማሸነፍ መቻሉንም ገልፀዋል። ድሉ የመጨረሻ አለመሆኑንም አንስተዋል።

ጠላትን እስከመጨረሻው #ማጥፋት እንደሚገባም ተናግረዋል። ጠላቶችን እስከመጨረሻው #ለማጥፋት የአማራ ክልል በትጋት እየሠራ እንደሆነ ያላቸውን እምነትም ገልፀዋል። የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያውያን እርስ በርሳቸው እንዲለያዩ የአንዱ አቅም ሌላኛውን እንዳይጠቀም ማድረጉንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ስትነካ አንድ ኾነው ተነስተዋል ያሉት። የቁስ ውድመት በቁስ ይተካል የሰብዓዊ ጉዳት ግን በምንም ሊተካ አይችልም፣ ያደረሰው ጉዳት አሳዛኝ ነውም ብለዋል።

ጠላቶቻችን አንገት እንድንደፋ ፈልገዋል እኛ ይሄን አንፈቅድም ፣ እኛ ጦርነቱን እንደ እድል ተጠቅመን ብርሃኑን ብቻ እያየን መጓዝ አለብን ነው ያሉት። የወደሙ ከተሞቻችን የውስጥ ኃይልን በመጠቀም እና ከተሞችን በማስተሳሰር የበለጠ አድርጎ መገንባት እንደሚገባም ገልጸዋል።

የወደሙ ከተሞችን የተሻሉ አድርገን እናቋቁማቸዋለንም ነው ያሉት።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርም ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን በአማራ ክልል ለተጎዱ ዜጎች ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል። የተጎዱ ከተሞችን ሌሎች ከተሞች እንዲደግፏቸው ከተሞችን እያስተሳሰሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

በአማራ ክልል ከተሞች የመስክ ተሽከርካሪና የቆሻሻ ማንሻ አምስት ዘመናዊ መኪናዎችን መሰጠቱን ገልጸዋል። ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተለያዩ ድጋፎችን ለክልሉ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

150 ሚሊዮን ብር ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ድጋፍ ማድረጋቸውንም አስታውቀዋል። ድጋፉ ቀጣይነት እንዳለውም ተናግረዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የአማራ ክልል ለዘመናት ያካበተው ሀብት በመዘረፉና በደል ስለደረሰበት ሕዝቡ ልቡ ተነክቷል ነው ያሉት። የወራሪው ቡድን ዋና ዓላማ ኢትዮጵያን ማደህየት፣ ማፍረስና ኢትዮጵያውያንን ማለያየት እንደሆነም ገልፀዋል። ጥቃቱ የመላው ኢትዮጵያውያን በመሆኑ ኢትዮጵያውያን በጋራ ተነስተው ጠላት ደምስሰዋል ነው ያሉት። ጦርነቱ አሁንም አለመቋጨቱንም አስታውቀዋል።

ጠላትን ለደመሰሱ ጀግኖች ምስጋና ይገባቸዋም ብለዋል። አሁንም ጀግኖች እየተፋለሙ መሆናቸውን አንስተዋል። ድሉ ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ያቆመ ወርቃማ ድል መሆኑንም ተናግረዋል።

ከነበረው የተሻለ አድርጎ ለመገንባት የሚያስችል እድል ያመጣ፣ የአማራ ክልል ሕዝብ ደራሽ ወገን እንዳለው ያረጋገጠበት እድል ነውም ብለዋል። መላ ኢትዮጵያውያን ከጎናችን እንደሆኑ አረጋግጠናልም ነው ያሉት። መቆዘምና መተከዝ ሳይኖር መሥራት እንደሚገባም አሳስበዋል። በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ለተደረገው ድጋፍም አመስግነዋል። የተደረገውን ድጋፍ በአግባቡ መጠቀም አለብን ነው ያሉት። ሌሎች ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችም ሀገርን የሚያፀና ሥራ እንዲሠሩ ጠይቀዋል። የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው በኢትዮጵያውያን መሆኑንም ተናግረዋል።

ድጋፉን ላደረጉት እንግዶችም ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለተፈናቃይ ወገኖች 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ድጋፍ አደረገች፡፡
Next article“እንደ ሰለሞን እንደ ሲራክ፣ እንደ ደጉ ንጉሥ እንደ ምኒልክ፣ መች ተጽፎ ያልቃል የኮስትር ታሪክ”