
ጎንደር፡ ጥር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሩጫ ውድድሩን አስመልቶ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ደመላሽ አበበ በሰጡት መግለጫ ፋሲል ከነማን ለማጠናከር በየዓመቱ የሙዚቃ እና የባዛር ዝግጅት እንደሚካሄድ ተናግረዋል። የዚሁ አካል የሆነው ታላቁ ሩጫ በርካታ እንግዶች እና የክለቡ ደጋፊዎች በተገኙበት የፊታችን እሑድ ጥር 8/2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡
ጎንደር ከተማ በጥምቀት ሰሞን ከምታከናውናቸው ታላላቅ ኹነቶች መካከል አንዱ የሆነው የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ማጠናከሪያ የሩጫ ውድድር ከጎንደር የጥምቀት በዓል ጋር በማስተሳሰር ይካሄዳል፤ ይህም የስፖርት ቱሪዝምን የማነቃቃት ዓላማ እንዳለው ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡ በዚህም በየዓመቱ ከጥምቀት በዓል በፊት ባለው እሑድ ቀን የሚካሄደውን የሩጫ ውድድር በሂደት ዓለም አቀፍ አትሌቶች የሚሳተፉበት እና ትኩረት የሚሰጠው ውድድር ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ከ10 ሺህ በላይ ሕዝብ እንደሚሳተፍበት የሚጠበቀው ‹‹ለአሸናፊዎች እሮጣለሁ›› የሩጫ ውድድር ከገቢ ማስገኛነት እና ከቱሪዝም ጥቅሙ ባሻገር በስፖርታዊ እንቅስቃሴ የተገነባ ጤናማ ማኅበረሰብን መፍጠርን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ነው ያብራሩት፡፡
‹‹ለአሸናፊዎች እሮጣለሁ›› የሚለው የዘንድሮው መሪ ቃል የተመረጠው ፋሲል ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ መንገድ ተደራጅቶ መካሄድ የጀመረበትን የመጀመሪያ ዓመት ዋንጫ በአሸናፊነት በመውሰዱ እና ኢትዮጵያ በድል ጎዳና እንደምትራመድ ለማመላከት መሆኑን የደጋፊዎች ማኅበር ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ- ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ-ከጎንደር
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/