ሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

89

ደሴ፡ ጥር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሰዎች ለሰዎች የተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ውድመት ለደረሰበት የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ከ8 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣል የተባለው የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በደረሰበት ዘረፋና ውድመት የተሟላ አገልግሎት እየሰጠ አይደለም። ሆስፒታሉ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ይችል ዘንድም የሁሉንም ኢትዮጵያውያን እና አጋር አካላት ርብርብ ይጠይቃል።

ዛሬ የሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

የድርጅቱ በኢትዮጵያ ተወካይ ይልማ ታዬ በአማራ ክልል ለደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጨምሮ ለሌሎች ስምንት ሆስፒታሎች 25 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡ በቀጣይም ድርጅቱ፥ በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ ተቋማትን በአዲስ መልክ ለመገንባት ያላሰለሰ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል፡፡

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ኃይማኖት አየለ የሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት ያደረገላቸው ድጋፍ ያለባቸውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር በተወሰነ ደረጃ የሚቀርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሌሎች ግለሰቦች እና ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅቶችም ተመሳሳይ ድጋፍ እዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ በክልሉ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከቀድሞው የተሻለ እና የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህንን ለማገዝ የሰዎች ለሰዎች ድርጅት ላደረገው ድጋፍም ምሥጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ፡- አሊ ይመር -ከደሴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Mudde 30/2014 ALI
Next articleለፋሲል ከነማ ማጠናከሪያ ‹‹ለአሸናፊዎች እሮጣለሁ›› የተሰኘ ታላቅ ሩጫ በጎንደር ከተማ ለአራተኛ ጊዜ የፊታችን እሁድ ጥር 8 ይካሄዳል፡፡