በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ የተመራ ልዑክ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና በተላላኪው ኦነግ ሸኔ የደረሰውን ጉዳት ተመለከተ።

106

ከሚሴ፡ ጥር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ልዑኩ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችን ያካተተ ነው፡፡ የሃይማኖት አባቶች በስፍራው ለተገኘው ልዑክ፥ አሸባሪዎቹ አካባቢውን በወረራ ይዘው በነበሩበት ወቅት ያደረሱትን ጉዳት አስረድተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሽዴ በብሔረሰብ አስተዳደሩ በመዘዋወር የተመለከቱት ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የጤና ተቋማት እና የትምህርት ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት ቢደርስባቸውም ወደ ሥራ እንዲመለሱ መደረጋቸውን አድንቀዋል። በቀጣይም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ነው የተናገሩት።

የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም በበኩላቸው በብሔረሰብ አስተዳደሩ የወደሙ ሃብቶችን መልሶ ለመገንባት ከክልሉ መንግሥት ጋር በቅንጅት እንደሚሠሩ አስረድተዋል።

በብሔረሰብ አስተዳደሩ የደረሰውን ጉዳት ከመስክ ጉብኝት በተጨማሪ በፎቶ አውደ ርዕይና በዘጋቢ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ለእይታ መቅረቡም ታውቋል።

ዘጋቢ፡- ይማም ኢብራሂም-ከከሚሴ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ እና የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት ዲያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠየቀ፡፡
Next articleMaxxansa Gaazexaa Hirkoo Mudde 30/2014 ALI