
ጥር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የ2014 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ በሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ ተጀምሯል። በዞኑ በዘንድሮው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ መከናወን ስላለባቸው ተግባራት አስቀድሞ ዝግጅት ተደርጓል ብሏል የዞኑ ግብርና መምሪያ።
የመምሪያው ኃላፊ ኤልያስ አበበ የዞኑ አርሶአደር በአንድ እጁ ነፍጥ በሌላኛው እጁ የልማት መሳሪያ አንስቶ ጠላቱን እየተፋለመ በግብርና ልማቱም ሲሳተፍ ቆይቷል ብለዋል። ዛሬ በተጀመረው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራም በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች በንቅናቄ ውጤታማ ሥራ ይሠራል ብለዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ታደሰ ገብረፃድቅ በበኩላቸው ካሁን በፊት የተሠሩት የአፈርና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች ከፍተኛ ውጤት አስገኝተዋል ነው ያሉት። የአርሶአደሩን ምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ እስከ ገበያ ፍጆታ የደረሰ ምርት እንዲገኝ አድርጓልም ብለዋል። የዞኑ ሕዝብ በጠላቱ የትግራይ ወራሪ ቡድንና ሸኔ ላይ በአንድነት እንደተነሳ ሁሉ በሚያከናውናቸው የልማት ተግባራትም ውጤታማ ሥራ ሊያከናውን ይገባል ነው ያሉት።
የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራው የተጀመረበት የአሳግርት ወረዳ ካሁን ቀደም በሥራው ከፍተኛ ውጤት ያመጣ እንደሆነም ተገልጿል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ዘነበ ኃይሉ የወረዳው መልከዓምድር አስቸጋሪ ቢሆንም በተጠና መንገድ የአፈርና ውኃ ጥበቃ በመሥራታችን የአርሶ አደሩን ህይወት መቀየር ችለናል ብለዋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው የወረዳው አርሶአደሮች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራው ውጤታማ እንዲሆን ጠንክረን እንሠራለን ብለዋል።
ዘጋቢ:- ኤልያስ ፈጠነ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/