
ጥር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በአጣዬ ከተማ በአሸባሪዎቹ የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ሽኔ የወደሙ የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ከስድስት ሚሊዬን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።
የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አሳልፍ ደርቤ እንደተናገሩት በሽብር ቡድኖቹ ከ250 በላይ ንጹሐን ተጨፍጭፈዋል። 420 መኖሪያ ቤቶች፣ 50 ግሮሰሪና ሆቴሎች ወድመዋል ብለዋል።
ዛሬ የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት በአማራ ልማት ማኅበር አስተባባሪነት ዘጠኝ መኖሪያ ቤቶችን በ6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጭ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።
የፈረሱ ቤቶችን የመገንባት ሥራው ይቀጥላል ያሉት የኢትዮጵያ ካናዳውያን ኔትወርክ ለማኅበራዊ ድጋፍ በጎ አድራጎት ድርጅት ምክትል ፕሬዚዳንት ማርቆስ ተገኝ ተጨማሪ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ ተይዟል ብለዋል።
የአማራ ልማት ማኅበር የዋና ሥራ አስፈጻሚ ልዩ ረዳትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አበረ መኩሪያ ዳያስፖራው የደረሰውን ጉዳት ለሌሎች በማሳወቅ ከተሞችን መልሶ ለመገንባት ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- ለዓለም ለይኩን
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/