
አዲስ አበባ፡ ጥር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ እንዳሉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር በስልክ ውይይት አድርገዋል። ይህ ውይይት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን የስልክ ውይይቱ የፖለቲካ ሁኔታው እየተቀየረ ስለመሆኑ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ነው ያሉት።
በሳምንቱ የዲያስፖራ አንቅስቃሴ ላይ ትልልቅ መድረኮች እንደተካሄዱም አብራርተዋል። የፓን አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴን ለማሳደግ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ብቻ ሳይሆኑ አፍሪካውያንም ተሳትፈውበታል ብለዋል። ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ዲያስፖራው ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር መምከሩንም አምባሳደር ዲና አስረድተዋል።
የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም ሚናቸውን በሚያሳድጉበት ዙሪያም ምክክር መደረጉን የተናገሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ዲያስፖራው በላልይበላ የልደት በዓልን እንዳከበረ ሁሉ አሁንም በጎንደር ጥምቀትን ለመታደም በርካታ ዝግጅቶች እንደተደረጉ ነው የገለጹት። ይህም ፀረ ኢትዮጵያ ኀይሎች ይነዙት የነበረውን የሀሰት ወሬ ትርጉም አልባ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:–አንዱዓለም መናን- ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/