
ባሕር ዳር፡ ጥር 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ አደም ወርቁ የተደረገው ድጋፍ በሽብር ቡድኑ የወደሙ መሥሪያቤቶች ሥራ እንዲጀምሩ ያስችላቸዋል ብለዋል።
ድጋፉ የተደረገው ከተሞች ለከተሞች በሚል ሀሳብ እንደሆነ ያስረዱት ኀላፊው ድጋፉን ያስተባበረው የክልሉ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ነው ብለዋል። በምዕራብ አማራ የሚገኙ 9 ከተሞች በምሥራቅ አማራ ለተጎዱ 9 ከተሞች የተለያየ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው አቶ አደም የተናገሩት።
የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊው እንዳሉት ዘጠኙ ከተሞች 3 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ ያደረጉ ሲኾን ቢሮው ለተጎዱ 4 የዞን መምሪያዎች፣ ሁለት አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ከተሞች 2 ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር በላይ የሚገመት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፎቹ ኮምፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ ለጽሕፈት የሚያገለግሉ መሣሪያዎችና ሌሎችም ቁሳቁስ ያካተተ መሆኑን የገለጹት አቶ አደም ድጋፉ የመጀመሪያ ዙር እንደሆነ አመላክተዋል።
ሁሉም ዜጎች በሽብር ቡድኑ ምክንያት የወደሙና የተዘረፉ መሰረተ ልማቶችን ለማቋቋም በሚደረገው ርብርብ ላይ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ኀላፊው ጠይቀዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው መሥሪያ ቤቶች ሠራተኞች በተለይ በዚህ ወቅት በቁጭት ሊሠሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/