
ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የሀገራቸውን ጥሪ ተከትለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ዲያስፖራዎች በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ በችግር ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን እና ሕፃናትን በዘላቂነት ለማቋቋም በሚያስችሉ እንቅስቀቃሴዎች ዙሪያ ተወያይተዋል።
የአማራ ክልል ሴቶች ሕፃናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ አስናቁ ደረስ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።
ጉዳቱ በሴቶች እና ሕፃናት ላይ የከፋ ነው ያሉት ኀላፊዋ እነዚህን ተጎጅዎች በዘላቂነት ለማቋቋም እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ከኖርዌ የመጡት ወይዘሮ ሰዋሰው ስለሽ በሴቶች እና በሕፃናት ላይ
ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ወይዘሮ ሰዋሰው ጉዳቱ በደረሰ ጊዜ ለአማራ እና ለአፋር ክልል የዕለት ደራሽ እርዳታ አድርገናል ብለዋል፡፡ ወይዘሮ ሰዋሰው ‟ሀገራችንን ስንረዳ ራሳችንን እንደረዳን እየቆጠርነ ነው የምንረዳ“ ነው ያሉት፡፡ ኢትዮጵያን ለማጠልሸት የሚሠሩ ሚዲያዎች መረጃቸው የሀሰት መሆኑን ለመግለጽ መሠራቱን የገለጹት ወይዘሮ ሰዋሰው በዚህም የተወሰነ ለውጥ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡
ወይዘሮ ሰዋሰው በችግር ውስጥ ያሉ ሕፃናት እና ሴቶችን ለማየት እና ለመርዳት መምጣታቸውን ተናግረዋል፤ ሚዲያዎች ዜናዎችን በተለያዩ ቋንቋዎች በመሥራት ተደራሽ የሚሆንበት መንገድ ቢመቻች ሲሉም ጠይቀዋል፡፡
በቀጣይም ያዩትን እና የሰሙትን በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ወዳጆች በማድረስ እና አንድ ዲያስፖራ ለአንድ ቤተሰብ የሚለውን አካሄድ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡
አቶ ያለው ታረቀኝ ኢትዮጵያውያን በውጭ በሚኖሩበት ጊዜ በርካታ ሥራዎችን መሥራታቸውን ነው የተናገሩት፡፡ አቶ ያለው ሴቶች እና ሕፃናትን እንዲሁም አካል ጉዳተኞች ለመደገፍ በሚደረገው ርብርብ የራሳቸውን ኀላፊነት እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡ አቶ ያለው ልጃቸው የሠጣቸውን 10 ሺህ ብር በመጨመር በየዓመቱ 20 ሽህ ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውም ታውቋል፡፡
ከሀገረ ኖርዌ የመጡት የኢትዮጵያ ማኅበር በኖርዌ ሠብሳቢ ልዑል ዓለማየሁ ታደሰ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እየሠራው ያለውን ሥራ ለማጋለጥ ሥራዎችን ሲሠሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡ ‟በሀገረ ኖርዌ ያለን ኢትዮጵዊያን ቁጥራችን ትንሽ ቢሆንም ጠላቶቻችን በሚነዙት የተሳሳተ መረጃ በኢትዮጵያ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ለማድረግ ዘመቻዎችን በማስተባበር ኀላፊነታችንን ተወጥተናል በቀጣይም ለመሥራት ዝግጁ ነን“ ብለዋል፡፡ ሌሎች በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆችም ከሀገሪቱ ጎን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አቶ ልዑል ዓለማየሁ የሀሰት ዜና ለማክሸፍ እና ከሀገራችን ጎን በመቆም የድርሻችንን ለመወጣት መጥተናልም“ ነው ያሉት፡፡ አቶ ልዑል በቆይታቸውም በችግር ላይ ለነበሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ጠቁመው በቀጣይም በችግር ውስጥ ላሉ ሕፃናት እና ሴቶች አብረዋቸው ከሚኖሩ ሰዎች ጋር በመወያየት ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሠሩ ጠቁመዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/