በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ተላላኪው ሸኔ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመተካት እና በብሔረሰብ አስተዳደሩ ለማልማት እንደሚሠሩ ባለሃብቶች አስታወቁ፡፡

139

ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ የተመራው ልዑክ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በመገኘት በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ተላላኪው ሸኔ የደረሰውን ውድመት ተመልክተዋል። ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የደረሰውን ጉዳት መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ሥራ ጉልህ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

በጉብኝቱ ላይ ሌሎች ባለሃብቶችና ዲያስፖራዎች የተገኙ ሲሆን በብሔረሰብ አስተዳደሩ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸውም ገልፀዋል።

በብሔረሰብ አስተዳደሩ የተቋቋመው መልሶ ማቋቋም ኮሚቴ አስተባባሪና የአደጋ መከላከል ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ መሐመድ ይማም በብሔረሰብ አስተዳደሩ የደረሰዉ ጉዳት የከፋ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ በአስተዳደሩ ኢንቨስት ለሚያደርጉ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታዎች እንደሚመቻቹም ገልፀዋል።

ዘጋቢ፡- ይማም ኢብራሂም

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
Next articleʺየጠላቶችህ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ የክተት ዘመቻ እንደተጠራህ አስብ”