የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

162

ጥር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል ከአገልግሎት ውጭ ኾነው ለነበሩ መሰረተ ልማቶች እና የወደብ ማሽነሪዎች አስፈላጊውን ጥገና በማድረግ፣ የሰው ኃይል፣ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶችን እንዲሁም አስፈላጊ ግብዓቶችን አሟልቶና እንደገና አደራጅቶ ከሰኞ ጥር 2/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል፡፡

በኮምቦልቻ ከተማ ያሉ የኢንዱስትሪ ተቋማት ከደረሰባቸው ጉዳት ተላቀው ወደ ሥራ እየተመለሱ ወደቡ ወደ አገልግሎት መመለስ አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች እና ልዩ ልዩ ግብዓቶች በፍጥነት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ በማስቻል ምርታማነታቸውን ለማስቀጠል ወሳኝ ሚና አለው ተብሏል፡፡

ይህንን ለማድረግም ድርጅቱ ለእነዚህ ተቋማትና ደንበኞች ዕቃቸው በፍጥነት ተጓጉዞ ሀገር ውስጥ የሚገባበትን ልዩ ሁኔታ ያመቻቸ መሆኑን ከድርጅቱ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የዘረፈውንና ያወደመውን ንብረት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እያጠና መሆኑን የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ አስታወቀ።
Next articleበሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን እና ተላላኪው ሸኔ የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመተካት እና በብሔረሰብ አስተዳደሩ ለማልማት እንደሚሠሩ ባለሃብቶች አስታወቁ፡፡