አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የዘረፈውንና ያወደመውን ንብረት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እያጠና መሆኑን የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ አስታወቀ።

229

ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ እየተካሄደ የሚገኘውን ጥናት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫውን የሰጡት የአማራ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ኀላፊ አንሙት በለጠ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል መጠነ ሠፊ የሰብዓዊ ጥሰት፣ የንብረት ዘረፋና ውድመት ፈጽሟል ብለዋል።

በሽብር ቡድኑ ምክንያት የደረሰውን አጠቃላይ ውድመት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እየተጠና እንደሆነ አቶ አንሙት አስረድተዋል። በጥናቱ መሠረት ትክክለኛ ውድመቱ እንደሚገለጽ ነው የተናገሩት። ጥናቱ በጎደለው ልክ ለመሙላት አጋዥ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

ከጥናቱ በኋላ የወደሙ መሰረተ ልማቶች ተመልሰው በሚገነቡበት ሁኔታ ላይም ስትራቴጂክ እቅድ እየተዘጋጀ እንደሆነ አመላክተዋል። አቶ አንሙት እንደተናገሩት የጥናቱ ዓላማ ቡድኑ ያደረሰውን ውድመት ትክክለኛ መረጃን መስጠትና በሰነድ ማስቀመጥ፣ የሽብር ቡድኑ ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግና ለመልሶ ጥገናው ሁኔታዎችን ማመቻቸት ነው።

በተለይ ዲያስፖራው በሚደረገው የመሰረተ ልማት መልሶ ጥገና ላይ ድጋፍ እንዲያደርግ፣ የጉዳቱን መጠን በሄደበት ቦታ ሁሉ እንዲያጋልጥ ከፍተኛ ኀላፊነት ይጠበቅበታል ብለዋል። ዲያስፖራው ረጂ ድርጅቶች በቀጥታ ድጋፍ እንዲያደርጉ የማስተባበር ተግባር እንደሚጠበቅበትም አስገንዝበዋል።

ዲያስፖራው የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በመጠቀም እራሱንና የተጎዳውን ክልል ማሳደግ ይጠበቅበታል ነው ያሉት። ለዚህም የተለያዩ የልማት አማራጮች ለዲያስፖራው እየተዘጋጀ መሆኑን ኀላፊው ገልጸዋል። ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ ድረስ ከ15 መሥሪያቤቶች ከየዘርፉ የተውጣጡ ባለሙያዎች በጥናቱ መሳተፋቸውንም ኀላፊው አስረድተዋል።

ከክልሉ መንግሥት እውቅናና ፈቃድ ውጭ ማንኛውም አካል ጥናት ማድረግ እንደማይችል አቶ አንሙት አሳስበዋል። ጥናቱ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንም ገልጸዋል።

ለጥናቱ ስኬታማነት ሁሉም ኅብረተሰብ ተባባሪ እንዲሆን ኀላፊው ጥሪ አድርገዋል።

ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous article❝ለሠራዊቱ አባላት የተሰጠው የማዕረግ እድገትና ሽልማት በደጀንነት የተሰለፈው ሕዝብ ላበረከተው አስተዋጽኦ እውቅና የሰጠ ነው❞ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Next articleየኮምቦልቻ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት ጀመረ።