
አዲስ አበባ: ጥር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በመግለጫቸዉ አሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ ቡድን የሀገር መከላከያ ሠራዊቱ እንዲበተን ለማድረግ ቢጥርም በመከላከያ ኀይል ህልሙ እዉን ሳይሆን መቅረቱን አንስተው ለዚህም ምሥጋና እና እዉቅና ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ይገባል ብለዋል። ይህ ሀገራዊ ድል የተገኘዉ ሺህዎች ሕይወታቸዉን ሰዉተዉ ነዉ ሲሉ ጠቅሰዋል። በአጭር ጊዜ ብቃት ያለዉ ተቋም መገንባት እንደሚቻል የመከላከያ ሠራዊቱ ማሳያ እንደሆነም ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
ዶክተር ለገሰ እንዳሉት ኢትዮጵያ የዘመነ የመከላከያ ሠራዊት ኀይል እየገነባች ትገኛለች፤ በዚህ ጦርነትም ዋጋ ለከፈሉ ጀግኖች የመጨረሻዉን የጥቁር አንበሳ እና የዓድዋ ሜዳይ ሽልማት በመንግሥት ተሰጥቷል፡፡
የተወሰኑ እስረኞችን ክስ የማቋረጥ ሂደት ላይ መግለጫ የሰጡት ዶክተር ለገሰ መንግሥት ሀገራዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ እንዲያግዝ ክሳቸዉ እንዲቋረጥ አድርጓል ብለዋል። የሀገር ሉዓላዊነትን እና አንድነትን ለማስቀጠል እንደሚረዳም አስገንዝበዋል።
በደብረ ጽዮን የክስ መዝገብ ስር ተይዘዉ ክሳቸዉ የተቋረጠው ከሰሜኑ ጦርነት ጋር ግንኙነት ያልነበራቸዉ እና በጤና ምክንያት እክል ያለባቸዉ መሆናቸዉንም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል። መንግሥት ይህንን ዉሳኔ ለማሳለፍ የቻለዉ ሀገራዊ ደኅንነትን ለማረጋገጥ ሲሆን ዉሳኔው ለሰላም እና ለጠንካራ ሀገር ግንባታ የሚያግዝ ነዉ ብለዋል። መንግሥት ለዉሳኔዎቹ ሙሉ ለሙሉ ኀላፊነቱን አንደሚወጣ ጠቅሰዉ በአካታች ምክክሩ ላይም ትኩረት ሰጥቶ ይሠራልም ብለዋል።
በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ እገዳ የተደረገባቸዉ የአሸባሪው ቡድን አባላት ንብረቶቻቸዉ ሊመለሱባቸዉ ነዉ እየተባለ የተሰራጨዉ መረጃ ከእዉነት የራቀ መሰረተ ቢስ ነዉ።ይህም የሕዝብ ሀብት ነዉ ብለዋል።
አሸባሪዉ የትግራይ ወራሪ ቡድን ለዳግም ወረራ እየተዘጋጀ መሆንን የጠቀሱት ሚኒስትሩ መንግሥት አሁንም የሽብር ቡድኑ ጥቃት ለማድረስ በሞከረባቸዉ አካባቢዎች እርምጃ ወስዷል ሲሉ ገልጸዋል። አሁንም የጥምር ኃይሉ ጸንቶ ቆይ በተባለበት አካባቢ ላይ በተጠንቀቅ ሀገራዊ ግዴታዉን እየተወጣ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ፡-ኤልሳ ግኡሽ – ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/