
ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስካልተወገደ ድረስ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ ስለማይቀር መቼም ቢሆን በድል ሰክረን አንተኛም ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ ገለጹ።
ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም አድማሱ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እስካልተወገደ ድረስ የኢትዮጵያ ስጋት መሆኑ አይቀርም። የሽብር ቡድኑ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ስለማይተኛ እኛም መቼም ቢሆን በድል ሰክረን አንተኛም ብለዋል።
ጦርነት ለሽብር ቡድኑ የመኖርና ያለመኖሩ ጉዳይ ስለሆነ ከዚህ በኋላም ቢሆን ወረራ ለማካሄድ ሊሞክር ይችላል ያሉት ሜጀር ጄነራል ሙሉዓለም፤ የሽብር ቡድኑ በአሁኑ ጊዜ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና በመሳሪያ ተዳክሟል፤የሞራል ውድቀትም ደርሶበታል ነው ያሉት።
በተቃራኒው በወገን ኃይል የድል ባለቤት በመሆኑ የበለጠ መነሳሳትና ወኔ ተፈጥሯል፣በቂ ዝግጅትም ተደርጓል፤ ከአሁን በኋላ የሽብር ቡድኑ ከስህተቱ ሳይማር ቀርቶ ወደ አፋርም ሆነ አማራ ክልሎች እስፋፋለሁ ቢልም እሳት ይጠብቀዋል ብለዋል።
አሸባሪው ሕወሓት ኢትዮጵያን ለመበታተንና መንግሥትን ለመጣል ዕቅድ ይዞ ያለ የሌለ ኃይሉንና የቀበረውን መሳሪያ አሰባስቦ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ያደረገው መፍጨርጨር መና እንደቀረና በጀግናው መከላከያ ሠራዊትና በጥምር የጸጥታ ኃይሎች ተቀጥቅጦና ድባቅ ተመትቶ ወደ ኋላ መመለሱን መግለፃቸውን የዘገበው ኢፕድ ነው።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/