
ደብረብርሃን፡ ጥር 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ ባለፉት 6 ወራት 1 ነጥብ 1 ሚሊዬን ዶላር የዉጭ ምንዛሬ ሲያስገኝ 20 ሚሊዬን ዶላር የሚያወጣ ምርትን በሀገር ዉስጥ ምርት መተካት መቻሉ ተገልጿል፡፡
የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ ሥራ አሥኪያጅ የሽጥላ ሙሉጌታ ፓርኩ በአስቸጋሪ ጊዜ ዉስጥ ሆኖም ምርቱን ሳያቋርጥ ማምረቱ ምጣኔ ሃብቱን በመደጎም አስተዋፅዖዉ የጎላ ነበር ብለዋል፡፡
የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ የማምረት ተግባሩን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲከዉን ያደረጉ ነዎሪዎች፣ የሥራ ኀላፊዎች እና የካምፓኒ ባለቤቶች እዉቅናና ሽልማት ተደርጎላቸዋል፡፡
የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንዱስትሪ ፓርክ ክትትል እና ድጋፍ መምሪያ ኀላፊ አቶ ብርሃን አለምነህ የደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ የዉጭ ምንዛሬን በማስገኘት የጎላ ሚና እያበረከተ እንደሆነ ተናግረው የአካባቢዉ ማኅበረሰብ የእኔነት ስሜት ለሌሎች ፖርኮች ምሳሌ መሆን የሚችል ነዉም ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ብርቱካን ማሞ-ከደብረ ብርሃን
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq በዌብሳይት amharaweb.com በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/