በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አደረጉ።

118

ባሕር ዳር፡ ጥር 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዲያስፖራ አባላቱ በቀጣይም የዘማች ቤተሰቦችን በቋሚነት ለመደገፍ ዝግጁ መኾናቸውን አስታውቀዋል።

የድጋፉ አስተባባሪ አቶ ማንደፍሮ ደምለው እንዳሉት በአሜሪካ ካሊፎርኒያ የሚኖሩ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ለ15 የዘማች ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው ለበዓል መዋያ 5 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል። ግለሰቦቹ ለበዓል መዋያ አኹን ላይ ድጋፍ ቢያደርጉም በቀጣይ አንድ ዲያስፖራ አንድ ቤተሰብ በቋሚነት ለመደገፍ ቃል መግባታቸውን ነግረውናል።

አቶ ማንደፍሮ እንዳሉት አጋዥ የሌላቸውን የዘማች ቤተሰቦች በተለያዩ አካባቢዎች በመለየት ነው ድጋፍ የተደረገው።

ሌላው ኢትዮጵያዊም ችግር ውስጥ የወደቁ የዘማች ቤተሰቦችን በመደገፍ ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የዘማች ቤተሰቦችም ልጆቻቸው ችግር ውስጥ በኾኑበት ወቅት ድጋፍ መደረጉ ኢትዮጵያዊያን ከጎናቸው ለመኾናቸው ማሳያ እንደኾነ ገልጸዋል። ለተደረገላቸው ድጋፍም አመስግነዋል።

ዘጋቢ:–ዳግማዊ ተሠራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleየኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች የጥቆማ ጊዜ እንዲራዘም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አቀረበ፡፡
Next articleየደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ ከውጭ የሚገባውን ምርት በሀገር ውስጥ በመተካት ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ማስቀረቱ ተገለጸ፡፡