የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች የጥቆማ ጊዜ እንዲራዘም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አቀረበ፡፡

224

ጥር 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች የጥቆማ ጊዜ እንዲራዘም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ኢዜማ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ ነው ጥያቄውን ያቀረበው፡፡ የሀገራዊ ምክክር አዋጁ ረቂቅ ላይ ማኅበረሰቡም ሆነ ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ውይይት እና ክርክር ሳያደርጉበትና በበቂ ሁኔታ ግብዓት ሳይታከልበት በፍጥነት ለፓርላማ ቀርቦ እንዲጸድቅ መደረጉ የሂደቱን ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ እንዳያስገባው ስጋት እንዳለው የገለጸፀው ኢዜማ፣ ሀገራዊ ምክክሩ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡ ሀገራዊ ምክክሩ በቂ ትኩረት እንዲያገኝ መደረግ ያለባቸውን ምክረ ሐሳቦችም ሰንዝሯል፡፡

«ማኅበረሰቡ በሌሎች በርካታ አጀንዳዎች ላይ ተጠምዶ በመክረሙ በሀገራዊ ምክክሩ አጠቃላይ ፋይዳና ሂደቱ ላይ በቂ የሆነ ግንዛቤን የማስጨበጥ ሥራ መሥራት ያስፈልጋል።» በማለት ስለ ሀገራዊ ምክክር ሂደት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራ መሥራት እንደሚገባ በደብዳቤው ጠቅሷል፡፡

የብዙኀን መገናኛዎች በሀገራዊ ምክክሩ ላይ የሕዝብን ተሳትፎ ከማጎልበትና ከማንቃት አንጻር ተገቢውን ሚና እየተጫወቱ እንዳልሆነ የገለጸው ኢዜማ፣ ብዙኀን መገናኛዎች ለምክክሩ ሂደት ትኩረት በመስጠት ለሀገርና ለሕዝብ ያላቸውን ወገናዊነት እንዲያሳዩ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የኮሚሽነሮች ጥቆማ ሂደት ውስብስብነት የሚታይበት መሆኑን ያነሳው ኢዜማ፣ በማያሻማ ሁኔታ ጥቆማ እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል ለሕዝቡ ግልፅ ማድረግ እንደሚገባ ጥያቄውን አቅርቧል፡፡

ከፖለቲካው ገለልተኛ የሆኑና ብቃት ያላቸውን ዜጎች ለመምረጥ እንዲያስችል ከታኅሣሥ 26/2014 ዓ.ም እስከ ጥር 06/2014 ዓ.ም ለኮሚሽነሮች ጥቆማ የተሰጠው የጊዜ ገደብ በቂ አለመሆኑን በደብዳቤው ላይ የገለጸው ፓርቲው፣ «የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በአዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት የጥቆማውን ጊዜ እንዲያራዝመው» በማለት የጥቆማው ጊዜ እንዲራዘም ምክረ ሐሳቡን አቅርቧል፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleበሕወሃት የተቀበሩ የአማራ እውነታዎችን የሚያጋልጥ መጽሐፍ ተዘጋጀ፡፡
Next articleበውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለዘማች ቤተሰቦች ድጋፍ አደረጉ።