በሕወሃት የተቀበሩ የአማራ እውነታዎችን የሚያጋልጥ መጽሐፍ ተዘጋጀ፡፡

377

ባሕር ዳር፡ ጥር 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ‹‹የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የታፈኑ እውነታዎች›› የተሰኘ መጽሐፍ በአማራ ክልል የሚገኙ በከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ፎረም አማካኝነት ተዘጋጅቷል፡፡ የዚህ መጽሐፍ ይዘት በወልቃይት፣ በጠገዴና በጠለምት የማንነት ታሪካዊ ዳራ እና ተጋድሎ ላይ የሚያተኩር ነው፡፡

በሕወሃት የተቀበሩ የአማራ እውነታዎች ይታወቁ ዘንድ ጥናቶችን መሠረት ባደረገ መልኩ ቀርቧል፡፡ መጽሐፉ ታሪካዊ ማጣቀሻዎችን፣ የሰው ማስረጃ እና ልዩ ልዩ ሰነዶችን ዋቢ በማድረግ የተዘጋጀ ነው፡፡ የአማራ ሕዝብና የኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት አመሠራረትም ሰፊ ዳሰሳ የተደረገበት ነው፡፡ የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት አስተዳደራዊ ታሪካዊ ዳራ በማጣቀሻ ተተንትኖበታል፡፡ አሸባሪው ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ያራመደው የጥፋት ፖለቲካ እና መነሻውን ደደቢት በርሃ ያደረገው አውዳሚ የፖለቲካ ስሪቱን በተመለከተም በጥልቀት ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡

ከባሕል፣ ከቋንቋ እና ከሥነልቦና ቅኝቶች አንጻር ሕወሓት በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት የፈጸማቸውን በደሎችና እውነታዎች የሚዳስስ ነው፡፡ የወልቃይት፣ የጠገዴና የጠለምት አማራን ባሕል፣ ወግ፣ ሃይማኖት እና ማኅበራዊ እሴት ለማጥፋት የተፈጸሙ ድርጊቶችንም ይፋ አድርጓል፡፡ በወልቃይት፣ በጠገዴና በጠለምት ሕዝብ ላይ አሸባሪው ህወሃት በኢኮኖሚው ዘርፍ የፈጸማቸውን ብዝበዛዎች ቁልጭ አድርገው የሚያሳዩ እውነታ በማስረጃ ቀርበዋል፡፡

ወልቃይት የአማራ ማንነነት ጥያቄ እና ጥያቄውን ተከትሎ እስከ አማራ ዘር ማጥፋት የደረሰውን ወንጀል በስፋት ይዳስሳል፡፡ ሕወሃት በሕዝብ እና በሀገር ላይ የፈጸመው ክሕደትም ተብራርቶበታል፡፡ ይህ መጽሐፍ በድኅረ ነጻነት እውነታዎች ሕዝቡ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና ለአማራ ጸጥታ ኃይል የሰጠውን ድጋፍ፣ የተጎናጸፋቸውን መብቶች እና በሕወሃት ላይ ያለውን ግልጽ አቋም ተዳስሶበታል፡፡

በትምሕርት እና በቋንቋ ዘርፎች በአማራ ላይ የተሠሩ ደባዎችን ከተበዳዩ ውጪ ያለ ሕዝብ እውቅና እንዲኖረው የተሰነደ ነው፡፡ መጽሐፉ ትውልዱን ከማስተማር ባለፈ ለታሪክ ማጣቀሻነት ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡

በሥርዓተ ትምሕርት ተካትቶ እንደ አንድ የማስተማሪያ ስልት መጠቀም ይቻላልም ተብሏል፡፡ በዘጠኝ ምዕራፎች ከሚያነሳቸው አንኳር ሀሳቦች በተጨማሪ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ፣ ለኢፌዴሪ መንግሥት፣ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ለትግራይ ሕዝብ (በተለይም ለልሂቃኑ) ጠቃሚ ምክረ ሀሳቦችን አስቀምጧል፡፡

መጽሐፉ በአረብኛ ቋንቋ ተተርጉሞ መዘጋጀቱን የፎረሙ ዋና ጸሐፊ ዶክተር አስማረ አብራርተዋል፡፡ በእንግሊዘኛ የመተርጎም ተግባርም ተጀምሯል ብለዋል፡፡ በ233 ገጾች የተጠረዘው ይህ መጽሐፍ በቅርቡ ተመርቆ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡ የአንድ መጽሐፍ መሸጫ ዋጋ 200 ብር ሲሆን ከሽያጭ የሚገኘው ገንዘብም ሙሉ ለሙሉ በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት አካባቢዎች ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ የሚውል ይሆናል ተብሏል፡፡

መጽሐፉ በቀጣይም ከአንባብያን የሚያገኛቸውን ሂሶች ዋቢ በማድረግ በስፋት ይታተማል ተብሏል፡፡ ይሕን መጽሐፍ እንደ አማዞን ባሉ ዓለም አቀፍ የመጽሐፍ ሽያጭ ማዕከላት ጭምር ለገበያ ለማቅረብ መታቀዱንም አመላክተዋል፡፡

በቀጣይ የራያን ጉዳይ በስፋት የሚዳስስ መሰል መጽሐፍ ለመጻፍ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ዶክተር አስማረ ደጀን ገልጸዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ደጀኔ በቀለ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/

Previous articleዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ጥምረት ለመከላከያ ሠራዊት ከ500 ሺህ ብር በላይ የሆኑ ለሕክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
Next articleየኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች የጥቆማ ጊዜ እንዲራዘም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ አቀረበ፡፡