
ጥር 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው “ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ዳያስፖራዎች ጥምረት” በተወካዮቻቸው አማካኝነት ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ግምታቸው ከ500 ሺህ ብር በላይ የሆኑ ለሕክምና አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶችና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
ድጋፉን ያስረከቡት የጥምረቱ ተወካይ መምህር ኮከብ ገዳሙ ፣ መንግሥት ለዳያስፖራው ያቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው መምጣታቸውን ገልጸዋል።
ከ27 ሀገራት የተውጣጣ የዳያስፖራ ማኅበራት የጥምረቱ ተወካዮች በጦርነቱ የተጎዱ ቦታዎችን በመጎብኘት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለኅብረተሰቡ ሲያደርጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል።
ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ድጋፍ መደረጉንም ተናግረዋል።
የዳያስፖራዎች ተግባር ምክር ቤት ጊዜያዊ ሥራ አስፈፃሚ ሊቀመንበር አቶ ዓለማየሁ አበበ በበኩላቸው ፣ ያለ ዳያስፖራው ተሳትፎ ዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች ተፈላጊውን ግብ እንደማይመቱ ገልፀዋል። ይህንኑ ለማጠናከር ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ውጤታማ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ጠቅላላ አገልግሎት ሎጀስቲክስ ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ሰብለ ሙሉጌታ ፣ የጥምረቱ አባላት ከዚህ በፊት “እንቁጣጣሽን ከሠራዊት ጋር” በሚል መርህ ከ200 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል። የጥምረቱ አባላት በጎ ተግባራቸውን በማጠናከር ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/