
ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ያቀረቡትን ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ አማራ ክልል ለመጣችሁ ዲያስፖራዎች በሙሉ፡፡
ሃገራችንን በዲፕሎማሲ ረገድ ለመደገፍ ያደረጋችሁትን ትግል የክልላችን መንግስት በእጅጉ ያደንቃል፡፡ ኃላፊነታችሁ ቢሆንም ለፈፀማችሁት አኩሪ ገድል ከልብ እናመሰግናለን፡፡
በቀጣይም በአማራ ክልል በሚኖራችሁ ቆይታ በትህነግ ወራሪ ሃይል የደረሰብንን ሰብአዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳት ተገንዝባችሁ ወገኖቻችሁን እንድትደግፉ ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች አዘጋጅታችኋል፡፡
ከጥር 1-8/2014 ዓ.ም ድረስ በክልላችን በወራሪው የትግራይ ሃይል የደረሱ ጉዳቶች እና በቀጣይ የአማራ ክልል ለመገንባት ያሉ የኢንቨስትመንት እና ሌሎች የልማት ስራዎችን የያዘ በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ የቀድሞው ግዮን ሆቴል ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ የትብብር እና የአንድነት አውደ ርዕይ አቅርበናል እንድትታደሙ ተጋብዛችኋል፡፡
ጥር 7/2014 ዓ.ም ዕለተ ቅዳሜ ደግሞ የትብብር እና የአንድነት የጋራ የውይይት መድረክ ከዲያስፖራ ወገኖቻችን ጋር ይኖረናል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የካቢኒ አባላትም በእለቱ ተገኝተው ከእናንተ ጋር ውይይት ያደርጋሉ፡፡
በዚሁ እለትም የትብብር እና የአንድነት የጋራ ማዕድ ይኖረናል፡፡ በእለቱ ተገኝታችሁ ለቀጣይ የክልላችን የላቀ እድገት የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ እንጠይቃለን፡፡
ተደጋግፈን ክልላችንን አልቀን እንገነባለን!!
“ድል ለኢትዮጵያ”!