
ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አቶ መላኩ ፍስኃ ነዋሪነታቸው በካናዳ ነው፡፡ ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብለው ከመጡ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ናቸው፡፡ አቶ መላኩ በካናዳ የሚኖሩ ጓደኞቻቸውን በማስተባበር ባዋጡት ሁለት ሚሊየን ብር በዓልን ከወገን ጦር አባላት ጋር አሳልፈዋል፡፡
አቶ መላኩ በካናዳ የሚኖሩትን ዶክተር ጌታቸው ማዘንጊያ እና አቶ መላኩ ስዩም ጋር በመሆን በተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ የወገን ጦር አባላት ለልደት በዓል መዋያ ድጋፍ አድርገዋል። በቀጣይም ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባልና የካናዳ ነዋሪ የኾኑት መላኩ ፍስኃ በዓሉን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርኃግብር መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሽብር ቡድኑ ምክንያት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን መልሶ መገንባት እና የተጎዱ ወገኖችን መደገፍ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
ዳያስፖራው በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን የውጭ ሀገራት ጣልቃ ገብነት እንዲቆም እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል፡፡
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሽብር ቡድኑን #ለማጥፋት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን መደገፍ እንዳለበት አቶ መላኩ አስገንዝበዋል፡፡ ❝እኛ ወደ ኢትዮጵያ የመጣነው ለመዝናናት ሳይሆን ሀገርን የመገንባት ዓላማ ሰንቀን ነው❞ ብለዋል፡፡
መሰረታዊ ወታደር ደስታ አይተንፍሱ ዳያስፖራው ወገናችን በዓልን ከእኛ ጋር በማሳለፋቸው ደስተኛ አድርጎናል ብሏል። ዳያስፖራው በየወቅቱ ድጋፍ ስላደረገለንም እናመሰግናለን ነው ያለው፡፡
አስር አለቃ አዲስዓየሁ መኮንን ዳያስፖራው በየወቅቱ ድጋፍ ሲያደርግ እንደቆየው ኹሉ አሁንም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቃለች፡፡
የወገን ጦር አባል ኮሎኔል ተስፋዬ ኤፍሬም ሠራዊታችን ጠላትን #ደምስሷል ብለዋል። ዳያስፖራው “በቃ” ወይም #No More በሚል ንቅናቄ የኢትዮጵያን ከፍታ አረጋግጧል ነው ያሉት፡፡ ዳያስፖራው ለሀገሩ በተለያየ መስክ ድጋፍ እያደረገ ነው፤ ወደፊትም ይህ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
የዳያስፖራ አባላት በዓሉን ከሠራዊቱ ጋር ኾነው ስላሳለፉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በማይነቃነቅ መሰረት ላይ ሀገር ለማቆም ኹላችንም መተባባር አለብን ብለዋል፡፡
ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊት በመቀላቀል ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና ነጻነት መከበር የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ቡሩክ ተሾመ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/